ናጅላ በቱኒዚያም ሆነ በመካከለኛው ምስራቅ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸው ተብሏል
የቱኒዚያው ፕሬዝዳንት ካይስ ሳኢድ፤ ናጅላ ባውደን ረመዳንን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው ሾሙ፡፡
ናጅላ በቱኒዚያም ሆነ በመካከለኛው ምስራቅ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የቱኒዚያው ፕሬዘዳንት ተጨማሪ ባለስልጣናትን ከስራ አገዱ
ፕሬዝዳንት ካይስ አዲስ መንግስት ለማዋቀር በማሰብ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር መሾማቸውን ጽ/ቤታቸው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ይህን ያደረጉት መንግስታቸውን ካፈረሱ ከሁለት ወራት በኋላ ነው፡፡
አዲስ የተሰየሙት ጠቅላይ ሚኒስትር እና ፕሬዝዳንት ካይስ ሳኢድ ዛሬ ተገናኝተው መምከራቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
የቱኒዚያ ጠቅላይ ሚኒስተር ከኮቪድ ጋር ተያይዞ በተፈጠረው ሁከት ከስልጣናቸው ተነሱ
አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ከዚህ በፊት በሀገሪቱ ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ውስጥ የጥራት ዋና ዳይሬክተርነትን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ላይ ሲሰሩ እንደነበር ተጠቅሷል፡፡
የ 63 ዓመቷ ናጂላ በቱኒዚያ መዲና ቱኒዝ ብሔራዊ የመሐንዲሶች ትምህርት ቤት ፕሮፌሰር ሲሆኑ በጂኦ ሳይንስ ትምህርት ምርምር መስራታቸው ተገልጿል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሯ ስራ የሚጀምሩት ሀገሪቱ ቀውስ ላይ ባለችበት ወቅት እንደሆነም ነው የተዘገበው፡፡