የቱኒዚያ የባህር ሃይል 78 ስደተኞችን ከሞት መታደጉን አስታወቀ
ባለፉት 9 ወራት ብቻ 19 ሺህ 500 የሚጠጉ ስደተኛች ሜዲትራኒያን ባህርን ሲያቋርጡ በቁጥጥር ስር ውለዋል
ስደተኞቹ በአብዛኛው የባንግላዴሽ እና የግብፅ ዜጎች ናቸው ተብሏል
የቱኒዚያ የባህር ሃይል ከሀገሪቱ የባህር ዳርቻ ወደ አውሮፓ ሲሻገሩ የነበሩተንና የጀልባ መስመጥ የገጠማቸውን 78 ስደተኞችን ከሞት መታደጉን የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒሰቴር አስታወቀ።
ስደተኞቹ በአብዛኛው የባንግላዲሽ ዜጎች እሆኒ እድሜያቸው ከ12 እስከ 45 ዓመት ክልል ውስጥ የሚገኙ ግብጻውያን እንደሚገኙበትም ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ስደተኞቹ አቡ-ካማሽ ከተባለ ስፍራ ተነስተው በዛዋራ አቅራቢያ በሚገኘው ሊቢያ ድንበር አቋርጠው በጀልባ ሲጓዙ እንደነበረ ሚኒስቴሩ ገልጿል።
የስደተኞቹን ህይወት ለማትረፍ በተደገ ጥረት የአንድ ስደተኛ ህይወት ማፉን ያስታወቀው ሚኒስቴሩ፤ 78 ስደተኞችን ግን መታደግ መቻሉን አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ “ስደተኞቹ የባህር ድንበር አቋርጠው ወደ አውሮፓ አቅጣጫ ለመዝለቅ አስበው ነበር፤ ነገር ግን ጀልባቸው ከቱኒዚያ ሁለተኛዋ ስፋክስ ከተማ በስተደቡብ የባህር ዳርቻ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ችግር ገጥሟታል” ብሏል።
ስደተኞቹ ወደ ኤል-ኬትፍ ወደብ ተወስደው ለብሔራዊ ጥበቃ እንዲሁም የሟቹ ስደተኛ ግብፃዊ አስከሬን ለማዘጋጃ ቤት ባለስልጣናት ተላፎ መሰጠቱን አስታውቋል
በሊቢያ የሙአመር ጋዳፊን ከስልጣን መነሳት ተከትሎ ለ10 አመታት የዘለቀው ህገ-ወጥነት በባህር ወደ አውሮፓ ለመግባት ለሚሞክሩ ስደተኞች ዋና ኮሪደር እንደዲሆን አድርጎታል።
እንደ ሊብያ ሁሉ ቱኒዚያ ከጣሊያን ደሴት ላምፔዱሳ በ140 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ቁልፍ የመነሻ ቦታ መሆኗም ለስደተኞች ሌላኛዋ ተመራጭ መነሻ ስፍራ አድረጓታል።
እንደ የቱኒዚያ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ መብቶች መድረክ መረጃ፤ የቱኒዚያ የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች በዚህ አመት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ሜዲትራኒያን ባህርን ለማቋረጥ ሲሞክሩ የነበሩ ወደ 19 ሺህ 500 የሚጠጉ ሰዎችን በቁጥጥር ስር አውለዋል።
በሮማ እና ቱኒዝ መካከል በሕገ-ወጥ ስደት ላይ የሚደረገውን ጥረት ለማቀናጀት እና መረጃን ለመለዋወጥ ቀጥተኛ የግንኙነት መስመር በሰኔ ወር ከተቋቋመ ወዲህ አዝማሚያው መጨመሩንም ነው የመድረኩ መረጃ የሚያመለክተው።