ህዝበ ውሳኔው በመጪው ሃምሌ አጋማሽ ይካሄዳል ተብሏል
ቱኒዚያ ልታደርግ ባቀደቻቸው ህገ መንግስታዊ ለውጦች ጋር በተያያዘ ህዝበ ውሳኔን ልታካሂድ ነው፡፡
ፕሬዝዳንት ካይስ ሳኢድ ከታሰቡት ህገ መንግስታዊ ማሻሻያዎች ጋር በተያያዘ መግለጫን ሰጥተዋል፡፡
ህዝበ ውሳኔው በፈረንጆቹ በመጪው ሃምሌ 25 እንደሚካሄድ አስታውቀዋልም፡፡
እስከ ህዝበ ውሳኔው መዳረሻ ከጥር እስከ መጋቢት ባሉት ወራት ምክክሮች እንደሚደረጉም ገልጸዋል ፕሬዝዳንት ካይስ፡፡
“ሃገሪቱ በበላተኞች እጅ እንዳትወድቅ ለማድረግ መውሰድ የሚገባኝን እርምጃ ነው የወሰድኩት” ሲሉም ተናግረዋል እርምጃቸውን ሲኮንኑ ለነበሩ አካላት ምላሽ በሚመስል መልኩ፡፡
የፓርላማ አባላትን ያሰሩት የቱኒዚያው ፕሬዚዳንት “አምባገነን አልሆንም” አሉ
ህዝበ ውሳኔው በከፊል በይነ መረብ እንደሚካሄድና ፓርላማው ህዝበ ውሳኔው ተጠናቆ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ እንደተበተነ እንደሚቆይ አስታውቀዋል፡፡
የህዝብን ሃብት ዘርፈዋል በሚል ከወቀሷቸው የንግዱ ማህበረሰብ አባላት ጋር እርቅ እንደሚያወርዱና ባለሃብቶቹ በልማት የተጎዱ የሃገሪቱን አካባቢዎች የሚደግፉበት ሁኔታ እንደሚመቻችም አብራርተዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ቱኒዚያ ለፀጥታው ምክር ቤት ያቀረበችው ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ እንዲደረግ ኢትዮጵያ ጠየቀች
የፓርላማ ምርጫው ከአንድ ዓመት በኋላ በመጪው ታህሳስ ነው እንደሚካሄድ የሃገሪቱ ብዙሃን መገናኛዎች ዘገባ አመልክቷል፡፡
ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ከወራት በፊት በሃገሪቱ ተቀስቅሶ ከነበረው ከፍተኛ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጭምር ያሰሩት ፕሬዝዳንት ካይስ አዲስ መንግስት ለማዋቀር በማሰብ በእርሳቸው ይመራ የነበረውን መንግስት አፍርሰው የአስፈጻሚነቱን ስልጣን ጠቅለው ይዘዋል፡፡
ናጅላ ባውደን ረመዳንን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርገው መሾማቸውም ይታወሳል፡፡