በቱኒዝያ አንድ ሐኪም ለወሊድ አገልግሎት የመጣች ታካሚን በቀጥታ ስርጭት ማስተላለፏ በርካቶችን አስቆጥቷል
የወሊድ ምጥን በቲክቶክ ቀጥታ ስርጭት ያስተላለፈችው ሐኪም
ስሟ ልተጠቀሰች አንድ ቱኒዝያዊት ሐኪም በምጥ ተይዛ ወደ ሆስፒታል ያመራችን እናት በቲክቶክ ቀጥታ ስርጭት አስተላልፋለች፡፡
ጉዳዩ በሀገሪቱ መነጋገሪያ አጀንዳ የሆነ ሲሆን በርካቶች የሐኪሟን ድርጊት ተችተዋል፡፡
የቱኒዝያ ሐኪሞች ማህበር ክስተቱን ያወገዘ ሲሆን በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ማጣራት እንደሚያደርግ እና እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል፡፡
የሀገሪቱ ሐኪሞች ማህበር ሀላፊ ዶክተር ፉአድ ቡዙች እንዳሉት ጉዳዩ ህክምናው የሚያዋርድ እና የሙያ ስነ ምግባርን ያልተከተለ ነው ብለዋል፡፡
በምጥ የተያዘች እናትን ስታምጥ በቀጥታ ስርጭት ስተላለፈችው ሐኪም ማንነት መለየቱን የተናገሩት ዶክተር ፉአድ ጉዳዩ እየተመረመረ እና እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል፡፡
ትራምፕ በስልጣን ዘመናቸው እንዲታገድ የወሰኑበትን ቲክቶክ ተቀላቀሉ
የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ቱኒዝያዊያን በጉዳዩ ላይ ብዛት አስተያየታቸውን የገለጹ ሲሆን ራስህን ድንገት ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ልታገኘው ትችላለህ ሲሉ ጽፈዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የማህበራዊ ሚዲያ ሱስ ሁሉንም ክስተት ለማሰራጭት እድል መፍጠሩን በመጥቀስ ምጥን በቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ የተጋነነ የማህበራዊ ሚዲያ ሱስ መገለጫ ነውም ብለዋል፡፡
ያለ ታካሚዋ ፈቃድ ምጧን በቲክቶክ አሰራጭታለች የተባለችው ሐኪም ማንነት ከተለየ በኋላ ቃሏን እንድትሰጥ ጥሪ ተደርጎላታል የተባለ ሲሆን ትፋተኛ ሆና ከተገኘች የሙያ ፈቃድን እስከመንጠቅ የሚደርስ ቅጣት ሊተላለፍባት ይችላልም ተብሏል፡፡