ቱርክ የተቃውሞ ሰልፍን ተከትሎ ከስዊድን እና ፊንላንድ ጋር ልታደርግ የነበረውን ስብሰባ ሰርዛለች
ቱርክ ስዊድን ስቶኮሆልም የተካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ ከስዊድን እና ፊንላንድ ጋር በየካቲት ወር ልታደርግ የነበረውን ስብሰባ ላልተወሰነ ጊዜ ሰርዛለች።
በስዊድን የተካሄደው ሰልፍ በቱርክ ዘንድ መወገዙን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሮይተርስ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ቤልጄም ብራሰልስ በመጭው የካቲት ወር ሊካሄድ የነበረው ስብሰባ ተሰርዟል።
ስብሰባው የተሰረዘው በቱርክ ጥያቄ መሆኑን ዘገባው ጠቅሷል።
የቱርክ ፕሬዝደንት ቃል አቀባይ በዚህ ወር መጀመሪያ ይካሄዳል በተባለው ስብሰባ ላይ የአውሮፖ ህብረት ዋና ጸኃፊ ሰቶልተንበርግ ይገኛሉ ብለው ነበር።
ሮይተርስ የቱርክ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት ጠቅሶ እንዘገበው ቱርክ ስብሸባውን አራዘመች እንጅ አልሰረዘችም ተብሏል።
በስዊድን የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ የቱርክን ኘሬዝደንት የሚተች መሆኑ ቱርክ ሁለቱ ሀገራትን ወደ ኔቶ የመቀላቀል እቅድን ተቃውማለች።
ቀደም ሲልም ቱርክ ሁለቱ ሀገራት ያስጠለሏቸውን የኩረድ አሸባሪዎች አሳልፈው ካልሰጧት ኔቶን እንዲቀላወሉ እንደማትፈቅድ ስትገልጽ ቆይታለች።