ቱርክ በገንዘብ መውደቅ እና በኑሮ ደረጃ ላይ ያጋጠመውን የኢኮኖሚ ድቀት ለመደጎምም ለሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ አድርጋለች
ቱርክ ለጡረታ የሚያስፈልገውን የእድሜ መስፈርት አስወገደች።
የቱርክ ፕሬዝዳንት ረሲጵ ጣይብ ኤርዶጋን ለጡረታ የእድሜ መስፈርትን በማስወገድ ከ ሁለት ሚሊዮን በላይ ሰራተኞች ወዲያውኑ ጡረታ እንዲወጡ አስችለዋል።
ውሳኔው ምርጫ ለማካሄድ ስድስት ወር የማይሞላ ጊዜ ለቀራት ሀገር እርምጃው ጥያቄ አስነስቷል።
የኤርዶጋን ገዥው ኤኬ ፓርቲ በዋጋ ንረት የተሸረሸረውን ድጋፍ ለማግኘት ባካሄደው ዘመቻ በገንዘብ መውደቅ እና በኑሮ ደረጃ ላይ የተስተዋለውን ከፍተኛ ማሽቆልቆል ለመደጎም ባሳለፍነው ሳምንት ከፍተኛ የደመወዝ ጭማሪ አድርጓልም ተብሏል።
ቀደም ሲል የጡረታ እድሜ ለሴቶች 58 እና ለወንዶች 60 ዓመት እንደነበር ተገልጿል። አዲሱ አሰራር ምን ያህል ወጪ እንደሚያስወጣ እስካሁን ግልጽ ባይሆንም ሁለት ነጥብ 25 ሚሊዮን ሰዎች ወዲያውኑ ጡረታ ለመውጣት መብቃታቸውን ኤርዶጋን ተናግረዋል።
በአሁኑ ጊዜ በቱርክ 13 ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ጡረተኞች አሏት።
ሮይተርስ እንደዘገበው የሠራተኛ ቡድኖች ለተወሰኑ ዓመታት ዝቅተኛውን የእድሜ መስፈርት ሲቃወሙ ቆይተዋል። በምትኩ ሠራተኞች ጡረታ ለመውጣት ግዴታ የሆኑ የስራ ቀናትን እንዲያጠናቅቁ ጠይቀዋል።
ይህ እርምጃ በሰኔ ወር ከሚካሄደው ወሳኝ ምርጫ በፊት ለኤርዶጋን መልካም እይታ እንደሚሰጥ ታምኖበታል።
ኤርዶጋን በስልጣን ላይ በቆዩባቸው ሁለት አስርት ዓመታት የተቃዋሚዎችን ዘመቻ በበላይነት ሲቆጣጠሩ እና በቅርብ ጊዜ ውስጥ ደግሞ ከአስር ዓመታት በፊት የሀገሪቱ ገንዘብ ሊራ ከዶላር ጋር ሲነጻጸር በአንድ አስረኛ እንዲወርድ የረዳውን ያልተለመደ የምጣኔ-ሀብት ፖሊሲ አውጥተዋል።