ቱርክ የባህር ኃይሏን ወደ ሶማሊያ ልትልክ ነው
ይህ የሆነው የቱርክ ኢነርጂ ሚኒስቴር ቱርክ ሶማሊያ ውስጥ ጋዝ እና ነዳጅ ለመፈለግ የአሰሳ ቡድን በዚህ አመት መጨረሻ እንደምትልክ ካስታወቁ ከአንድ ቀን በኋላ ነው
የቱርኩ ፕሬዝደንት ታይፕ ኢርዶጋን የቱርክን ጦር ወደ ሶማሊያ ለመላክ እንዲፈቀድላቸው እቅዱን በትናንትናው እለት ለቱርክ ፓርላማ አቅርበዋል
ቱርክ የባህር ኃይሏን ወደ ሶማሊያ ልትልክ ነው
ሁለቱ ሀገራት፣ አንካራ በሶማሊያ የባህር ጠረፍ የነዳጅ እና ጋዝ ፍለጋ እንድታደርግ ከተስማሙ በኋላ ቱርክ ወደ ሶማሊያ የባህር ይዞታዎች የባህር ኃይሏን ልታሰማራ ነው።
የቱርኩ ፕሬዝደንት ታይፕ ኢርዶጋን የቱርክን ጦር በሀገሪቱ የውሃ ድንበሮች ጨምሮ ወደ ሶማሊያ ለመላክ እንዲፈቀድላቸው እቅዱን በትናንትናው እለት ለቱርክ ፓርላማ አቅርበዋል።
ይህ የሆነው የቱርክ ኢነርጂ ሚኒስቴር ቱርክ ሶማሊያ ውስጥ ጋዝ እና ነዳጅ ለመፈለግ የአሰሳ ቡድን በዚህ አመት መጨረሻ እንደምትልክ ካስታወቁ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።
በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ የሶማሊያ የመከላከያ ሚኒስትር በአንካራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ቱርክ እና ሶማሊያ የመከላከያ እና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።በቅርብ አመታት ቱርክ የሶማሊያ የቅርብ አጋር እየሆነች ነው።
ቱርክ ሶማሊያ ውስጥ ትምህርት ቤቶችን፣ ሆስፒታሎችን እና ሌሎች መሰረተልማቶችን ገንብታለች። ከዚህ በተጨማሪም ቱርክ በርካታ የሶማሊያ ተማሪዎች በቱርክ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እድሎችን ሰጥታለች።
በ2017 ቱርክ፣ ከግዛቷ ውጭ ትልቅ የተባለው ወታደራዊ ሰፈር የገነባችው ሶማሊያ፣ ሞቃዲሹ ውስጥ ነው።ቱርክ ለሶማሊያ ወታደሮች እና ፖሊሶች ስልጠና ትሰጣለች።
ኢትዮጵያ ሶማሊያ የግዛቷ አንድ አካል አድርጋ ከምታያት ሶማሊላንድ ጋር ባለፈው ታህሳስ ወር የወደብ ስምምነት መፈራረሟን ተከትሎ ሶማሊያ ከኢትዮጵያ ያላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተበላሽቷል።
በስምምነቱ ተበሳጭታ የኢትዮጵያን አምባሳደር እስከማባረር የደረሰችው ሶማሊያ ቱርክን ጨምሮ የተላለዩ ሀገራትን ድጋፍ ስታሰባስብ ነበር።
ቱርክም የሶማሊያ የግዛት አንድነት ሊከበር ይገባል ስትል ለሶማሊያ አጋርነቷን መግለጿ ይታወሳል።
በቅርቡ ደግሞ ቱርክ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ያለው ውጥር እንዲረግብ ለማድረግ የሁለቱን ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሮች በአንካራ አነጋግራለች።