የቱርኩ ፕሬዝደንት ዋነኛ የተናቃኝ በማህራዊ ሚዲያ ለተለቀቀው ሀሰተኛ ጽሁፍ ኃላፊነቱን ትወስዳለች ሲሉ ሩሲያን አስጠንቅቀዋል
ሩሲያ በቱርክ ምርጫ ጣልቃ ገብታለች የሚለው ክስ የተቀነባበረ ውሸት ነው ብላለች።
ክሬሚሊን በትናንትናው እለት እንዳስታወቀው ሩሲያ በቱርክ ምርጫ ጣልቃ ገብታለች የሚለው ውንጀላ ሀሰት እና የተቀነባበረ ውሸት ነው ብሏል።
የቱርኩ ፕሬዝደንት ዋነኛ የተናቃኝ የሆኑት ከማል ክሊክዶሮግሉ በማህራዊ ሚዲያ ለተለቀቀው ሀሰተኛ ጽሁፍ ኃላፊነቱን ትወስዳለች ሲሉ ሩሲያን አስጠንቅቀዋል።
የቱርክ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን በሁለት አስርት አመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ፉክክር እንደሚያጋጥማቸው የተነገረለት ምርጫ በነገው እለት ይካሄዳል።
የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ ሩሲያ ከቱርክ ጋር ላላት የሁለትዮሽ ግንኙነት ቦታ ትሰጣለች፤ ይህን ውንጀላም በፍጹም አትቀበለውም ብለዋል።
ፔስኮቭ እንደተናገሩት ሩሲያ ጣልቃ አትገባም ብለዋል
ለክሊክዳርጎሉ ሩሲያ ጣልቃ ገብታለች የሚል መረጃ ያደረሳቸው ካለ እሱ ውሸታም ነው ሲሉ ፔስኮቭ ተናግረዋል።
ኤርዶጋን በአንካራ በርካታ ደጋፊዎቻቸው በተሰበሰቡበት በተቃዋሚዎቻቸው ላይ ሽብርኝነትን እና የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን ይደግፋሉ የሚል ክስ አቅርበዋል።
ተቃዋሚዎች ደግሞ የግንባታ ደህንነት ደንብን በአግባቡ ባለማስፈጸማቸው ለደረሰው የርዕደ መሬት አደጋ ኤርዶጋን ኃላፊነት መውሰድ አለባቸው እያሉ እየተቿቸው ነው።