ከ64 ሚሊዮን በላይ መራጮች 192 ሽህ የሚጠጉ የምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ እየሰጡ ነው
በቱርክ በድጋሚ እየተካሄደ ባለው ፕሬዘዳናታዊ ምርጫ ቱርካውያን ፕሬዝዳንታቸውን እየመረጡ ነው።
በቱርክ ባለፈው ግንቦት 14 በተካሄደው ምርጫ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን እና ዋና ተቀናቃኛቸው ክሊክዳርጎሉ አብላጫ ድምጽ ማግኘት ባለመቻላቸው ምርጫው በድጋሚ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በምርጫው ከ64 ሚሊዮን በላይ መራጮች 192 ሽህ የሚጠጉ የምርጫ ጣቢያዎች ዛሬ ከማለዳው ጀምሮ ድምጽ እየሰጡ ነው።