ቱርክ በሀገሯ የሚንቀሳቀሱ የአሜሪካ ኩባንያዎችን ገንዘብ አገደች
አገሪቱ የተቋማቱን እና ግለሰቦችን ገንዘብ ያገደችው ሽብርተኝነትን ይደግፋሉ በሚል ነው
ገንዘባቸው ከታገደባቸው ተቋማት መካከል በቺካጎ የሚገኘው ኒያጋራ ፋውንዴሽን አንዱ ነው
ቱርክ የ770 ሰዎች እና የአሜሪካ ተቋማትን ገንዘብ አገደች።
ቱርክ ከ2016ቱ መፈንቅል መንግስት ጋር በተያያዘ ሽብርተኝነትን ይደግፋሉ በሚል መቀመጫቸውን አሜሪካ ያደረጉ የ770 ተቋማትን እና ግለሰቦችን ገንዘብ አግዳለች።
ከታዋቂው የሀይማኖት መሪ ፈቱላህ ጉለን ጋር በተያያዘ የ400 ግለሰቦችን ገንዘብ ያገደች ሲሆን ቀሪዎቹ ደግሞ ዋና መቀመጫዎቻቸውን በአሜሪካ የተለያዩ ከተሞች አድርገው በቱርክ የሚንቀሳቀሱ ተቋማት ናቸው።
በቱርክ መንግስት ገንዘባቸው ከታገደባቸው ተቋማት መካከል ዋና መቀመጫውን በቺካጎ በማድረግ በቱርክ የሚንቀሳቀሰው ኒያጋራ ፋውንዴሽን ዋነኛው መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧ።
የቱርክ መንግስት ከዚህ በተጨማሪ ከኩርዲስታን ሰራተኞች ፓርቲ እና ከአይኤስ የሽብር ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ 200 ሰዎች ገንዘብም እንዳይንቀሳቀስ ማገዱ ተገልጿል።
ቱርክ ከዚህ ቀደምም በውስጥ ጉዳዬ ጣልቃ ገብተዋል ያለቻቸውን የአሜሪካንን ጨምሮ የ10 ሀገራት አምባሳደሮች አገሯን ለቀው እንዲወጡ አዛ እንደነበረ ይታወሳል።
በወቅቱ አምባሳደሮቹ እንዲባረሩ የተወሰነው በፈረንጆቹ 2016 ዓመት ከተካሄደው እና ከከሸፈው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ጀርባ እጁ አለበት በሚል ተጠርጥሮ ጉዳዩ በፍርድ ሂደት ላይ ያለ አንድ ግለሰብ ከእስር እንዲፈታ መጠየቃቸውን ተከትሎ ነው።