ዩኤኢ፤ በቱርክ 10 ቢሊዮን ዶላር ኢንቨስት ልታደርግ ነው
የተባበሩት አረብ ኤሚሬት እና ቱርክ በ10 ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ተፈራርመዋል
የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ወደ አቡዳቢ ሊያቀኑ መሆኑን ገለጹ
የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ወደ አቡዳቢ ሊያቀኑ መሆኑን ገለጹ፡፡
ካቩሶግሉ በሚቀጥለው ወር አቡዳቢን እንደሚገኙ የቱርክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
የአቡዳቢ ልዑል አልጋወራሽ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (ዩኤኢ) ጦር ምክትል ጠቅላይ አዛዥ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ትናንት ረቡዕ ህዳር 15 ቀን 2014 ዓ/ም ቱርክን ጎብኝተዋል፡፡
የመሃመድ ቢን ዛይድ የነገ የአንካራ ጉብኝት…ለምን?
በቱርክ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኦርዶጋን ግብዣ አንካራን የጎበኙት ቢን ዛይድ ከፈረንጆቹ 2012 ዓመት በኋላ አንካራን የጎበኙ የመጀመሪያው መሪ ሆነዋል፡፡
ቢን ዛይድ በአንካራ ቆይታቸው ከቱርክ ጋር በጋራ ሊሰሩ የሚችሉባቸውን ስምምነቶች ተፈራርመዋል፡፡
ሁለቱ አገራት በጋራ ለመስራት ከተፈራረሙባቸው ጉዳዮች መካከል በሀይል ልማት፣ በንግድ፣ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር መከላከል፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በወደብ ልማት እና ሌሎች ይገኙበታል፡፡
ስምምነቶቹ የተፈረሙት የአቡዳቢ ልዑል አልጋወራሽ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (ዩኤኢ) ጦር ምክትል ጠቅላይ አዛዥ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን እና የቱርክ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኦርዶጋን የሁለትዮሽ ውይይቶችን ካደረጉ በኋላ ነው፡፡
በዚህ የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረትም የተባበሩት አረብ ኢምሬት 10 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የሚጠይቁ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን እንደምትተገብር በቢንዛይድ በኩል አስታውቃለች፡፡
ሁለቱ አገራት ከዚህ በተጨማሪም የሁለቱን አገራት የጋራ ጥቅሞችን ሊያስጠብቁ የሚችሉ ሌሎች ስምምነቶችን እንደሚያደርጉ የዩኤኢ የኢንዱስትሪ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ሱልጣን አል ጃቤር ተናግረዋል፡፡