አውሮፕላን አብራሪው የመንገደኞች አውሮፕላን በማብረር ላይ እያለ ህይወቱ አለፈ
ካፒቴን ኢሴሂነ ፔህሊቫን ንብረትነቱ የቱርክ አየር መንገድ የሆነ አውሮፕላን አብራሪ ነበር
አብራሪው ከአሜሪካዋ ሲያትል ወደ ኢስትንቡል ኤርባስ ኤ350 አውሮፕላን በማብረር ለይ እያለ ህይወቱ አልፏል
አውሮፕላን አብራሪው የመንገደኞች አውሮፕላን በማብረር ላይ እያለ ህይወቱ አለፈ፡፡
የ59 ዓመቱ ካፒቴን ኢሴሂነ ፔህሊቫን ንብረትነቱ የቱርክ አየር መንገድ የሆነ አውሮፕላን አብራሪ ነበር፡፡
ይህ አብራሪ ከአሜሪካዋ ሲያትል ወደ ኢስታንቡል በመብረር ላይ እያለ ህመም ከተሰማው ከጥቂት ጊዜ በኋላ ህይወቱ እንዳለፈ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ በበረራ ላይ የነበረው አውሮፕላን ረዳት አብራሪው ሃላፊነት በመውሰድ በመንገደኞች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ማድረጉን የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ ተናግረዋል፡፡
ቃል አቀባዩ ያህያ ኡስተን እንዳሉት "ለካፒቴኑ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታ ለማድረግ የተደረገው ጥረት አልተሳካቱን ተከትሎ ረዳት አብራሪው ወዲውኑ በድንገት በረራውን በማቋረጥ አውሮፕላኑን ወደ መሬት ለማሳረፍ እየተሞከረ እያለ ህይወቱ አልፏል" ብለዋ፡፡
ኤርባስ ኤ350 አውሮፕላኑ በኒዮርክ በድንገት ካረፈ በኋላ መንገደኞችን በመጫን ወደ ኢታንቡል የተጀመረው በረራ እንደቀጠለም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ሙሽሪት 3 ኪሎግራም ወርቅ ጥሎሽ ያገኘችበት አነጋጋሪው የቱርክ ሰርግ
አውሮፕላን አብራሪው ከፈረንጆቹ 2007 ጀምሮ የቱርክ አየር መንገድ አውሮፕላኖችን ሲበር ነበር የተባለ ሲሆን በየጊዜው የጤና ምርመራም ሲያደርግ ነበር ተብሏል፡፡
እስካሁን ለአብራሪው ህይወት ማለፍ ምክንያት ምን እንደሆነ ይፋ አልተደረገም፡፡ አየር መንገዱ እድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ ለሆኑ አብራሪዎች በየ 6 ወሩ የጤና ምርመራ ማስረጃ እንዲያቀርቡ የሚያስገድድ ህግ አለው፡፡
ከዚህ በፊት በፈረንጆቹ 2015 ላይ የአሜሪካ አየር መንገድ አብራሪ ከአሜሪካ ፎኒክስ ወደ ቦስተን በመብረር ላይ እያለ የ57 ዓመቱ አብራሪ በድንገት ህይወቱ አልፎ አውሮፕላኑም እንዲያርፍ ተደርጎ ነበር፡፡