ዩኤኢ በኢትዮጵያ የምታደርገውን ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክራ ቀጥላለች
ሰብዓዊ ድጋፎቹ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማህበሩ አስታውቋል
በኤምሬት የቀይ ጨረቃ ማህበር (ERC) በኩል የተላኩ ሰብዓዊ ድጋፎች ዛሬ አዲስ አበባ ደርሰዋል
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (ዩኤኢ) በኢትዮጵያ የምታደርገውን ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክራ ቀጥላለች፡፡
የኤምሬት የቀይ ጨረቃ ማህበር (ERC) ሰብዓዊ ድጋፍ ኢትዮጵያውያን እርዳታዎችን ማድረሱን ቀጥሏል፡፡
ማህበሩ ያስጫናቸው አዳዲስ የህክምና እና ጤና ግልጋሎቶችን ለመደገፍና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመግታት የሚያስችሉ ቁሳቁሶች ዛሬ አዲስ አበባ አበባ ደርሰዋል፡፡
“የዛሬው የዩኤኢ ድጋፍ ድንገተኛ ህክምናን ከማጠናከር አንጻር የሚመሰገን ነው”- ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ ጤና ሚኒስትር
ምግብ እና አልባሳትን ጨምሮ ሌሎች ሰብዓዊ ድጋፎችን ማድረሱን እንደሚቀጥልም ማህበሩ አስታውቋል፡፡
የኤምሬት የቀይ ጨረቃ ማህበር (ERC) ዋና ጸሃፊ ሞሃመድ አጢቅ አል ፈላሂ (ዶ/ር) ዩኤኢ የኢትዮጵያን ህዝብ መደገፏን እንደምትቀጥል ተናግረዋል፡፡
ሃገራቸው በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ጉዳዮች ቅድሚያ ሰጥታ እንደምትሰራም ነው ዋና ጸሃፊው የተናገሩት፡፡
ዩኤኢ ለትግራይ ክልል የሚሆኑ የምግብ እርዳታዎችን የጫነ አውሮፕላን ላከች
የአሁኑ ድጋፍ በወቅታዊ ሁኔታዎች ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ሴቶችንና ህጻናትን ለመደገፍ በሚል የተደረገ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል፡፡
ማህበራችን የኢትዮጵያን ሰብዓዊ ሁኔታዎች በቅርበት እየተከታተለ ድጋፍ ለማድረግ የሚደረጉ ጥረቶችን ይደገፋልም ነው ዋና ጸሃፊ ያሉት፡፡