በቱርክ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሁለቱ ተፎካካሪዎች ከ50 በታች ድምጽ በማግኘታቸው ምርጫው በድጋሚ እየተካሄደ ነው
በቱርክ በድጋሚ እየተካሄደ ባለው ፕሬዘዳናታዊ ምርጫ ቱርካውያን ፕሬዝዳንታቸውን እየመረጡ ነው።
በቱርክ ባለፈው ግንቦት 14 በተካሄደው ምርጫ ፕሬዝደንት ኤርዶጋን እና ዋና ተቀናቃኛቸው ክሊክዳርጎሉ አብላጫ ድምጽ ማግኘት ባለመቻላቸው ምርጫው በድጋሚ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በመጀመሪያ ዙር ምርጫ ላለፉት 20 ዓመታት ቱርክን የመሩት ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን 49.5 በመቶ እንዲሁም ተቀናቃኛቸው ክሊክዳርጎሉ ደግሞ 44.9 በመቶ ድምጽ ማግኘታቸው ይታወሳል።
በዚህም ከ50 በመቶ በላይ ያመጣ እጩ ባለመኖሩ ምርጫው በዛሬው እለት በድጋሚ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በቱርክ እየተካሄደ ባለው ምርጫ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ያለው እጩ ለፕሬዝደንት ኤርዶጋን ድጋፉን በመስጠት ዋና ተቀናቃኝ የሆኑት ከማል ክሊክዳርጎሉ የሚደርስባቸውን ፉክክር እንዲጠነክርባቸው አድርጓል።
የኩርዶች ደጋፊ የሆነው ኤችዲፒ ፖርቲ ክሊክዳርጎሉን የደገፈ ሲሆን የኩርዲሽ እስላሚስት ደግሞ ኤርዶጋንን ደግፏል።
ፕሬዝደንት ኤርዶጋን በመጀመሪያው ምርጫ ተቀናቃኛቸውን ክሊክዳርጎሉን ስለመሩ እድል ከሳቸው ጋር ነች የሚል ግምት ተሰጥቷቸዋል።
ክሊክዳርጎሉ ስድስት ፖርቲዎችን በያዘ ጥምረትና እና የኩርድ ፖርቲ በሆነው ኤችዲፒ ፖርቲ ይደገፋሉ።