ትዊተር የሰማያዊ ባጅ ወይም ቨርፊኬሽን በ8 ዶላር መስጠት ጀመረ
ክፍያውን የሚፈጽም ማንኛውም ሰው ወይም ኩባንያ ሰማያዊው ባጅ ይሰጠዋል ብለዋል ኤለን መስክ
ኩባንያው ሰማያዊ ባጅ ወይም ቨርፊኬሽን የሚሰጣቸውን ሰዎች ማንነት የሚያረጋግጥበት መንገድ ግን ግልፅ አይደለም
ትዊተር የሰማያዊ ባጅ ወይም ቨርፊኬሽን በ8 ዶላር መስጠት ጀመረ።
ኩባንያው በትናንትናው እለት መተግበሪያውን አሻሽሎ አገልግሎቱን መስጠት ጀምሯል፡፡
"በወር 7 ነጥብ99 ዶላር የሚከፍል ማንኛውም የትዊተር ደንበኛ እንደ ታዋቂ ሰዎች፣ ኩባንያዎች እና ፖለቲከኞች ሁሉ ከስሙ በኋላ ሰማያዊ ባጅ ይኖረዋል" ብለዋል ቢሊየነሩ ኤለን መስክ በትዊተር መልዕክታቸው።
የማህበራዊ ትስስር ገፁ ሰማያዊ ባጅ ወይም ቨርፊኬሽን የሚሰጣቸውን ሰዎች ማንነት የሚያረጋግጥበት መንገድ ግን ግልፅ አይደለም።
አገልግሎቱ በአሜሪካ፣ ካናዳ፣ አውስትራሊያ፣ ኒውዝላንድ እና ብሪታንያ የተጀመረ ሲሆን፥ በአጭር ጊዜ ውስጥ ህንድን ጨምሮ በመላው አለም እንደሚዳረስ ተገልጿል።
የግዙፉ የኤሌክትሮኒክ ተሽከርካሪዎች አምራቹ ቴስላ ባለቤት ኤለን መስክ ትዊተርን በ44 ቢሊየን ዶላር ከገዙ ከሳምንት በኋላ ነው ኩባንያው አዲሱን አሰራር የተገበረው።
የትዊተርን ሰራተኞች በግማሽ የቀነሱት መስክ ተጨማሪ ገቢ ማስገኛዎችን እንደሚተገብሩ መናገራቸውንም ሬውተርስ አስነብቧል።ትዊተር እንደ ዩትዩብ ሁሉ ለተጠቃሚዎቹ ገቢ የሚያስገኝበትን አሰራር የመዘርጋትና ሌሎች ማሻሻያዎችንም ጠብቁ ብሏል።