ትዊተር ይዘት ይከታተሉ የነበሩ በርካታ ሰራተኞችን ማባረሩ ስጋትን ፈጠረ
ኩባንያውን በ44 ቢሊየን ዶላር የገዙት ኢለን መስክ ቲዊተርን እያሻሻሉ መሆኑን ተናግረዋል
የዓለማችን ባለጸጋው ሰው በትስስር ገጹ ላይ የጥላቻ እና አድሎአዊ ይዘትን የሚከታተሉ በርካታ ሰራተኞችን ከወዲሁ አሰናብተዋል
ኢለን መስክ ትዊተርን በይዘት ይከታተሉ የነበሩ በርካታ ሰራተኞችን ከስራ ማሰናበታቸው ታውቋል።
መሊሳ ኤንግል የተባለች የቀድሞ ሰራተኛ ለዶቼ ቨሌ እንደተናገረችው በዚህ ምክንያት በማህበራዊ የትስስር ገጹ ጥቃት እንደሚጨምር እጠብቃለሁ ብላለች።
የኩባንያው “የሲቪክ ታማኝነት” ቡድን አባል በመሆኗ የተሳሳቱ የፖለቲካ መረጃዎችን ትቆጣጠር እንደነበር ገልጻለች።
ከብራዚል እስከ አሜሪካ የተደረጉ ምርጫዎች የተሳሳተ መረጃ ከገጹ ላይ በመከታተልና ተመሳሳይ ይዘትን ለመለየት ስልተ ቀመሮችን መጻፏን የቀድሞ ሰራተኛዋ ተናግራለች። ትዊተር ጤናማ መድረክ እንዲሆን መስራታቸውንም እንዲሁ።
ኩባንያው በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ካባረራቸው 3 ሽህ 700 የሚጠጉ ሰራተኞች በተጨማሪ መሊሳ ኤንግልን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች የኮንትራት ሰራተኞች ውላቸውን አቋርጧል።
ኩባንያውን በ44 ቢሊየን ዶላር የሸመቱት ኢለን መስክ ቲዊተርን እያሻሻሉ መሆኑን ተናግረዋል።
የዓለማችን ባለጸጋው ሰው በትስስር ገጹ ላይ የጥላቻ እና አድሎአዊ ይዘትን የሚከታተሉ በርካታ ሰራተኞችን ከወዲሁ አሰናብተዋል።
በአሁኑ ጊዜ በቲዊተር ውስጥ ምን ያህል ሰዎች በይዘት ማስተካከያ ጥረቶች ላይ እንደሚሰሩ ግልጽ አለመሆኑን የጠቀሰው ዶቼ ቨሌ የተግባቦት ቡድኑንም የበተነው ኩባንያው አስተያየት እንዲሰጥ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ አልሰጠም።
የኩባንያው ሰራተኞችን ማሰናበት ገጹ “አላግባብ መጠቀምን” እንደሚያመጣ እና የፍተሻ ስርዓቶች የበለጠ አስተማማኝ እንዳይሆን ሊያደርግ እንደሚችል ስጋት አድሯል።
የይዘት ተቆጣጣሪዎችን መቅጠር ወጪ ማስወጣቱ፤ ወጪ መቀነስ ላይ ለተጠመዱት ባለቤቱ ፍቱን መድኃኒት መስሎ ታይቷል።