የትዊተር ኩባንያ የአርትኦት ሳጥን ለማካተት ከባለፈው አመት ጀምሮ እየሰራ እንደነበረ አስታውቋል
የትዊተር ኩባንያ የአርትኦት ሳጥን(ኢዲት በተን) ለማካተት ከባለፈው አመት ጀምሮ እየሰራ መሆኑን እና የትዊተር ብሉ ባጅ ባለቸው ተጠቃሚዎች ላይ ሙከራ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
የትዊተር ብሉ ባጅ ያላቸው ተጠቃሚዎች በወር በሚያደርጉት ክፍያ ወይም ሰብስክሪፕሽን የትዊተርን ፕሪሚየም ፊቸሮችን (ለየት ያሉ ገጽታዎችን) እና የዘመኑ መተግበሪያዎችን ማግኘት እንደሚችሉ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የትዊተር የፍጆታ ምርቶች ሃላፊ የሆኑት ጄይ ሱሊቫን በትዊተር ገፃቸው ላይ ኩባንያው ካለፈው አመት ጀምሮ የአርትዖት አማራጭን ለመገንባት እየሰራ መሆኑን ተናግሯል፣ "ለበርካታ አመታት በጣም የተጠየቀውን የትዊተር ፊቸር"።
ባለፈው ሳምንት የተነገረው ይህ ዜና ኩባንያው ሰፊ የአቅጣጫ ለውጥ ሲገጥመው ባበብቱ ኢለን ማስክ ትልቁ ባለድርሻ ሆኖ ቦርዱን ተቀላቅሏል፡፡ ትዊትር እንሌሎቹ የማህበራዊ ሚዲያዎች ፌስቡክ፣ኢንስታግራም እና ቴሌግራም የተጫነ ጽሁፍን ኢዲት ለማድረግ የሚያስችል የአርትኦት ቁልፍ አልበረውም፡፡