ትዊተር በኢትዮጵያ ላይ ገደቦችን መጣሉን አስታወቀ
ከሰሞኑ ጥቂት የማይባሉ ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያው ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያን ‘አካውንት’ መዘጋቱ ይታወቃል
ትዊተር በኢትዮጵያ ስላሉ ወቅታዊ ጉዳዮች መረጃዎች የሚንሸራሸሩበትን ገጽ (ትሬንድስ) ለጊዜው መዝጋቱንም አስታውቋል
ትዊተር የማህበረሰብ ትስስር ተቋም በወቅታዊ ጉዳዮች ምክንያት በኢትዮጵያ ላይ ገደቦችን መጣሉን አስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ ያሉ ሁኔታዎችን በቅርበት እየተከታተልኩ ነው ያለው ተቋሙ ደህንነታቸው የተጠበቀ የመረጃ ልውውጦች እንዲኖሩ በትኩረት እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡
ግጭት ቀስቃሽ እና ሰብዓዊነትን የሚያጎድሉ ልውውጦች (ትዊትስ) ከሚመራበት ህግ እንደሚጣረሱም ነው ያስታወቀው፡፡
ይህንኑ ከግምት ውስጥ በማስገባት እና ሊደርሱ የሚችሉ አካላዊ ጉዳቶችን ታሳቢ በማድረግ በኢትዮጵያ ስላሉ ወቅታዊ ጉዳዮች መረጃዎች የሚንሸራሸሩበትን ገጽ (ትሬንድስ) ለጊዜው መዝጋቱንም ገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ ከሚፈጸመው የሳይበር ጥቃት 90 በመቶው በግንዛቤ ጉድለት የሚያጋጥም ነው
ይህ መሆኑ የማህበረሰብ ትስስር ገጹን ላልተገባ ዓላማ ለመጠቀም አሁንም ይደረጋሉ ያላቸው ጥረቶች ለማስቆም እንደሚበጅም አስታውቋል፡፡
እርምጃው ግጭት ለመቀስቀስና አካላዊ ጉዳትን ለማስተባበር የሚደረጉ ሙከራዎችን ለማክሸፍ ያስችላል የሚል እምነት እንዳለውም ነው የገለጸው፡፡
ትዊተር ከሰሞኑ ጥቂት የማይባሉ ታዋቂ የማህበራዊ ሚዲያው ተጠቃሚ ኢትዮጵያውያንን ‘አካውንት’ በመዝጋት እንቅስቃሴያቸውን እየገደበ ነው በሚል ሲነገር ነበር፡፡
የቀድሞው የዩኤስ ፕሬዝደንት ትራምፕ ፣ ናይጄሪያ ትዊተርን ማገዷን አደነቁ
በተለይ ስለ ኢትዮጵያ እና ስለ መንግስት ለመጻፍና ለመናገር የሚደፍሩ ጸሃፊዎችን አግዷልም ተብሏል፡፡ በተጨባጭ ያገዳቸው ገጾችም አሉ፡፡
ትዊተር ብቻ አይደለም ፌስቡክ ጭምር፤ በእንዲህ ዐይነት ተግባራት ላይ መሰማራቱን ‘አካውንታችን ተዘጋ፤ ቴክኒካዊ በሆነ መንገድ ተከታዮቻችን ጋር እንዳይደረስ ተደረገ’ በየሚሉ ብዙዎች ገልጸዋል፡፡
ፌስቡክ ከሰሞኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ልጥፎችን (ፖስት) ከይፋዊ ገጻቸው ጭምር ማንሳቱ ይታወሳል፡፡
ከአል ዐይን አማርኛ ጋር በነበራቸው ቆይታ “አንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ለፖለቲካ ሀይሎች መጠቀሚያ ሆነዋል፤ አሁን ባለንበት ሁኔታም ፌስቡክ እና ትዊተርን ለአብነት ማንሳት ይቻላል” ብለው የነበሩት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ዋና ዳይሬክተር ሹመቴ ይግዛው (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ፌስቡክን እና ትዊተርን ሊተካ የሚችልና ቢያንስ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጠቀም የሚስያችል ሀገራዊ የማህበራዊ ትስስር ገጽ የመተግበር እቅድ እንዳላት መናገራቸው የሚታወስ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ የለሙ ዋትሳፕና ዙምን የሚተኩ የተግባቦት ፕላትፎርሞች ሙከራ ተጠናቆ ወደ ስራ ሊገቡ መሆኑን መግለጻቸውም አይዘነጋም፡፡
በኢትዮጵያ ከ25 ሚልዮን የሚልቁ የዳታ እና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች እንዳሉ ከኢትዮ ቴሌኮም የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡