በሰሜን እስራኤል በሚገኘው የኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ የቦምብ ጥቃት ተፈጸመ
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ በዛሬው እለት በትዊተር ገጻቸው ክስተቱ "ሁሉንም ቀይ መስመሮች የጣሰ" ነው ሲሉ ጽፈዋል
ፖሊስ በመግለጫው ኔታንያሁም ይሁን ቤተሰቦቻቸው በቦታው አለመኖራቸውን እና የደረሰ ጉዳትም እንደሌለ ጠቅሷል
በሰሜን እስራኤል በሚገኘው የኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ላይ የቦምብ ጥቃት መፈጸሙ ተገለጸ።
በሰሜን እስራኤል ካሳሪያ ከተማ ወደሚገኘው የጠቅላይ ሚኒስቴር ቤንያሚን ኔታንያሁ መኖሪያ ቤት ሁለት ቦምቦች መወርወራቸውን እና ግቢ ውስጥ ማረፋቸውን ፖሊስ አስታውቋል።
ፖሊስ በመግለጫው ኔታንያሁም ይሁን ቤተሰቦቻቸው በቦታው አለመኖራቸውን እና የደረሰ ጉዳትም እንደሌለ ጠቅሷል።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ በዛሬው እለት በትዊተር ገጻቸው ክስተቱ "ሁሉንም ቀይ መስመሮች የጣሰ" ነው ሲሉ ጽፈዋል።
"ኢራን እና አጋሮቿ ለመግደል ዛቻ የሚያደርጉበትን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ከሀገር ውስጥ ለተመሳሳይ ዛቻ ሰለባ ሊሆን አይገባም" ብለዋል ካትዝ።
ካትዝ ሁሉም የጸጥታ እና የፍትህ አካላት አስፈላጊ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። የእስራኤል ፕሬዝደንት ኢስሀቅ ሄርዞግ ክስተቱን አውግዘው፣ ምርመራ እየተካሄደ ነው ብለዋል።
"በጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ላይ የተቃጣው ትንኮሳ ሁሉንም ወሰኖች የጣሰ ነው።
"በመኖሪያ ቤቱ ላይ ቦምብ መጣል ሌላ ቀይ መስመር የመጣስ ተግባር ነው"ሲሉ የተናገሩት ደግሞ የደህንነት ሚኒስትሩ ኢታማር ቤንጊቪር ናቸው።
ባለፈው ጥቅምት ወር በካሳሪያ በሚገኘው መኖሪያ ቤት ላይ የድሮን ጥቃት የተቃጣ ቢሆንም ጉዳት አላደረሰም ነበር።
የእስራኤል ጦር በሰሜን በኩል ከባለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ በኢራን ይደገፋል ከሚባለው የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላ ጋር የተኩስ ልውውጥ እያደረገ ይገኛል። ለቅዳሜው ክስተት ኃላፊነት የወሰደ አካል የለም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ኢራን በእስራኤል ላይ ቀጥተኛ የሆነ ጥቃት ካደረሰች ወዲህ የካቢኔ ስብሰባዎችን ጭምር ለደህንነታቸው በመስጋት ቦታ በመቀያየር እያደረጉ ናቸው።