ሁለት ጋዜጠኞች የ2021 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
ሽልማቱ ያሸነፉት ጋዜጠኞች ፊሊፕናዊቷ ማርያ ሬሳ እና ጀርመናዊው ዲመትሪ ሙርታቮ ናቸው
ጋዜጠኞች የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሲሆኑ እንደፈረንጆቹ ከ1935 ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ነው
የፊሊፕንስ እና ሩስያ ጋዜጠኞች የ2021 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ፡፡
ማርያ ሬሳ እና ዲመትሪ ሙርታቮ የተባሉት ፤ጋዜጠኖቹ በፊሊፕንስና ሩስያ ባለስልጠናት ባይወደዱም የዓለም አቀፉ የኖቤል ሸላሚ ኮሚቴ “ጋዜጠኞቹ ስጋት ውስጥ ሆነው በነጻነት የመናገርን መብት እንዲከበር ለከፈሉት ዋጋ ክብር ይገባቸዋል” በሚል የኖቤል የሰላም ተሸላሚ እንዲሆኑ መርጧቸዋል፡፡
የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ ኃላፊዋ በሪት ሬስ አንደርሰን ፡ “ማርያ እና ዲመትሪ በፊሊፕንስና ሩስያ ሃሳብን በነጻነት ለማግለጽ መብት እንዲኖር በሚል ላሳዩት ድፈረትና ቆራጥነት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል” ብሏል፡፡
" ጋዜጠኞቹ በዓለም ዙርያ በከባድ ሁኔታዎች ታጅበው በሙያቸው ለነጻነትና ዴሞክራሲ መከበር ዋጋ በመክፈል ላይ ያሉትን ጋዜጠኞች የሚወክሉ ናቸው"ም ብሏል በሪት ሬስ አንደርሰን፡፡
በሪት ሬስ አንደርሰን " ነጻ፣ገለልተኛ እና በእውንት ላይ የተመሪከዘ ጋዜጠኝነት በስልጣን መባለግ፣ ውሸቶች እና የጦርንት ፕሮፖጋንዳዎች ለመከላከል የሚያችል እንደሆነ"ም ተናግሯል፡፡
እንደፈረንጆቹ በ 1935 ጀርመናዊው ጋዜጠኛ ካርል ቮን ኦሴሴዝኪ የኖቤል ሽልማት ካሸነፈ ወዲህ ሽልማቱ ለጋዜጠኞች ሲሰጥ የመጀመሪያው ነው።
ጋዜጠኛ ካርል ቮን ኦሴሴዝኪ በወቅቱ ለሽልማት የበቃው “ጀርመን ከዓለም ጦርነት ማግስት እንደገና ጦር ወደ ማደራጀትና ማስታጠቅ ድብቅ ተግባር እየገባች እንደነበረች በማጋለጡ” ነው፡፡
የኖቤል የሰላም ሽልማቱ መስራቹ ስዊድናዊ አልፍሬድ ኖቤል ለማስታወስ በሚል ህይወቱ ባለፈበት ቀን ታህሳስ 10 የሚሰጥ ይሆናል፡፡ አልፍሬድ ኖቤል በፈቃዱ የነርዌይ የኖቤል የሰላም ሽልማት የመሰረተው እንደፈረንጆቹ በ 1895 እንደነበር ይታወቃል፡፡