የቤሩቱን ከባድ ፍንዳታ የሚመረምሩት ዳኛ ይነሱ በሚል ተቃውሞ ሳቢያ ሁለት ሰዎች ተገደሉ
ባለፈው አመት በተከሰተው ፍንዳታ በርካታ ሰዎች ሞተዋል
የሊባኖስ ጦር ግድያው የተፈጸመው ክርስቲያኖችንና የሺኣ ሙስሊሞችን መንደር በሚከፍለው ቦታ መሆኑን ገልጿል
ባለፈው ዓመት በከተማዋ ወደብ ላይ የፈነዳውን ፍንዳታ የሚመረምሩት ዳኛ እንዲነሱ በጠየቁ በሊባኖስ የሺዓ ቡድን ሂዝቦላ ደጋፊዎች ላይ በተከፈተተኩስ ቢያንስ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል።
ከፈረንጆቹ 1975-90 ባለው ጊዜ ሊባኖስ የእርስ በእርስ ግጭት ያሳለፈች ሲሆን በፍንዳታው ምርመራ ላይ የተፈረጠረው አለመግባባት በሀገሪቱ ያለውን ስር የሰደደ ክፍፍል እንደሚያሳይ ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የሊባኖስ ጦር በሰጠው መግለጫ የክርስቲያን እና የሺዓ ሙስሊም ሰፈሮችን በሚከፍለው አካባቢ በሚገኝ የትራፊክ ክበብ ውስጥ ተኩስ መከፈቱን አስታውቋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂም ሚካቲ ህዝቡ እንዲረጋጋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ግድያው የተጀመረው ክርስቲያኖች በሚኖሩበት መንደር መሆኑን ሮይተርስ ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
የሄዝቦላው አላማናር ቴሌቪዠንን ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው ሁለት ሰዎች መገደላቸውንና አምስት ሰዎች ደግሞ ቆስለው ወደ ሆስፒታል መላካቸውን ዘግቧል፡፡ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ሺኣ መሆናቸውን ዘገባው ጠቅሷል፡፡
ሮይተርስ የአይን እማኖችን ጠቅሶ እንደዘገበው ከሆነ ተኩሱ ለሰአታት የቆ እንደነበረና በሮኬት የሚወነጨፍ የቦንብ ፍንዳታም መኖሩን ተናግረዋል፡፡ የሊባኖስ ጦር ሰልፈኖች ክርስቲያኖችንና የሺኣ ሙስሊሞችን በሚከፍለው ቦታ ላይ ሲደርሱ ተኩስ እንደተከፈተባቸው በመግለጫው አስታውቋል፡፡
በቤሩት ተከስቶ በነበረው ከባድ ፍንዳታ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ217 በላይ ሰዎች ሲሞቱ 7ሺ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው ይታወሳል፡፡