ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት 51 ኢትዮጵያዊያኑን በጭነት መኪና ሲያዘዋውሩ ነው
የታንዛኒያ ፖሊስ 51 ኢትዮጵያዊያንን ሲያዘዋውሩ ነበር ያላቸውን ሁለት ታንዛኒያውያን ያዘ፡፡
ሁለት ታንዛኒያውያን 51 ኢትዮጵያዊያንን በህገ ወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ በፖሊስ መያዛቸው ተገልጿል፡፡
እንደ ሲጂቲኤን ዘገባ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማቅናት በሚል በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያኑ ከነ አዘዋዋሪዎቹ በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል፡፡
የታንዛኒያ ፖሊስ እንዳሳወቀው ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎቹ የተያዙት በዶዶማ ክልል በጭነት ተሽከርካሪ ውስጥ አድርገው ከታንዛኒያ ለማስወጣት ሲሞክሩ በህግ ቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ከወንጀሎቹ ጀርባ ክልሎች ተጨማሪ ወንጀሎችን ያከናውኑ መሆን አለመሆኑን ለማጣራት ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራዎችን እንደሚያካሂድም ተገልጿል፡፡
ታንዛኒያ ኢትዮጵያዊያን በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት የሚመርጧት መሸጋገሪያ አገር ስትሆን በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የተገኙ ኢትዮጵያዊያን በታንዛኒያ እስር ቤት ይታሰራሉ፡፡
የኢትዮጵያ መንግስትም ከታንዛኒያ አቻው ጋር በመነጋገር በየጊዜው በታንዛኒያ እስር ቤቶች ያሉ ዜጎችን ወደ አገራቸው በመመለስ ላይ ይገኛል፡፡