ሁለት የቴሌኮም ኩባንያዎች መጋቢት እና ሚያዚያ ላይ ገበያውን ይቀላቀላሉ ተባለ
ሁለቱ አሸናፊ የቴሌኮም ኩባንያዎች የ40 በመቶ ድርሻ እንደሚኖራቸው ባለስልጣኑ ገልጿል
ወደ ኢትዮጵያ ገበያ የሚገቡ ሁለቱ የቴሌኮም ኩባንያዎች በ15 ቀናት ውስጥ ይፋ ይደረጋሉ
ወደ ኢትዮጵያ ገበያ የሚገቡ ሁለቱ የቴሌኮም ኩባንያዎች በ15 ቀናት ውስጥ ይፋ ይደረጋሉ
ሁለት ዓለም አቀፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች በመጋቢት እና ሚያዚያ ላይ የኢትዮጵያን የቴሌኮሙኒኬሽን ገበያ እንደሚቀለቀሉ የኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን አስታወቀ፡፡
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ባልቻ ረባ ዛሬ የቴሌኮም ሴክተሩን በከፊል ወደ ግል ለማዘዋወር እየተካሄደ ስላለው እንቅስቃሴ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ኩባንያዎችን የመገምገም ሂደት ተጠናቆ ሲልቅ ኩባንያዎቹ በቀጥታ ወደ ገበያ እንደሚገቡ ያስታወቁት ዋና ዳይሬክተሩ ሁለቱ ብቃት ያላቸው ተጫራቾች በሚቀጥሉት 15 ቀናት ውስጥ ይፋ ይደረጋሉ ብለዋል ፡፡
በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቃታቸው የተረጋገጠና ደረጃቸውን የጠበቁ ኩባንያዎች እንዲሆኑ መስፈርት መቀመጡን ያነሱት አቶ ባልቻ የገንዘብ እና የቴክኒክ መስፈርቶችም ከጥራት ጋር የተቀመጡ መስፈርቶች ናቸው ብለዋል፡፡
ሁለቱ አሸናፊ የቴሌኮም ኩባንያዎች የ 40 በመቶ ድርሻ እንደሚኖራቸው መንግስት መወሰኑ የሚታወስ ሲሆን 12 ኩባንያዎች በመንግስት ባለቤትነት የተያዘውን የኢትዮ ቴሌኮምን 40 በመቶ ድርሻ ለመያዝ ፍላጎት ማሳየታቸው ይታወሳል፡፡ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ቮዳፎን፣ቮዳኮም፣ኤምቲኤን ፤ኢቲሳላት እና ሳፋሪኮም ይገኙበታል፡፡
የቴሌኮም ዘርፉን በከፊል ወደ ግል ለማዞር የታሰበው የዲጂታል ልማትን ለማሳደግ ፣ ደረጃውን የጠበቀ የቴሌኮም ኢንዱስትሪ ለመገንባት ፣ የዘርፉን የፋይናንስ አቅም ለማሳደግ እና የቴሌኮሙኒኬሽን ተደራሽነትን ለማሳደግ እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡