ሶማሊያ፣ የአሚሶም ምክትል ኃላፊ በሳምንት ውስጥ ከሃገሯ እንዲወጡ አዘዘች
ሞቃዲሾ፤ አሚሶም እና ተመድ የጋራ ተልዕኮ እና ስምሪት ይኑራቸው የሚለውን ስትቃወም ነበረ
ሲሞን ሙሎንጉ ሶማሊያን በሳምንት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት ከተልዕኳቸው ውጭ ሲንቀሳቀሱ በመገኘታቸው ነው
ሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሶማሊያ ተልዕኮ (አሚሶም) ልዩ ተወካይ በሰባት ቀናት ውስጥ ሞቃዲሾን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች፡፡
ሲሞን ሙሎንጉ ሶማሊያን በሳምንት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት በሃገሪቱ ከተሰማርቶ ከሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ሰላም አስከባሪ ጦር (አሚሶም)ም ሆነ ከሶማሊያ የደህንነት ጉዳዮች የሚቃረኑ ተግባራትን ሲፈጽሙ በመገኘታቸው ነው፡፡
ይህንንም የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በጻፈውና የልዩ ተወካዩን መባረር በገለጸበት ደብዳቤ አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ጉዳዩን በተመለከተ ያለውን ቅሬታ ደጋግሞ ለኮሚሽኑ የፖለቲካ፣ የጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች ቢሮ ማስታወቁን ገልጿል፡፡
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ፋርማጆ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብል “የዘገየውን ምርጫ” ለማካሄድ ተስማሙ
ሆኖም አጥጋቢ ምላሽ አለማግኘቱን ነው ያስታወቀው፡፡
ሞቃዲሾ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ በሶማሊያ የጋራ ተልዕኮ እና ስምሪት ይኑራቸው የሚለውን ስትቃወም ነበረ፡፡
አፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ “ሁሉም ወገኖች ተኩስ አቁመው ለውይይት እንዲቀመጡ” በድጋሚ አሳሰቡ
ከወር በፊት ሞቃዲሾ ከሚገኙ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የአሚሶም ልዑካን ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ግን ጣምራ የቴክኒክ ቡድኑ በጋራ መስራቱን እንዲቀጥል እና የተመድ ዋና ጸሀፊ ለጸጥታው ምክር ቤት ማቅረብ ለሚፈልጉት ሪፖርት ግብዓት በሆኑ አጋዥ ተግባራት እንዲያግዝ ስምምነት ላይ ተደርሶ ነበር፡፡
ሆኖም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና አሚሶም ሁኔታውን በተመለከተ ሶማሊያ የተካተተችበትን የጋራ ሪፖርት ለማውጣት አልፈቀዱም፤ ይልቁንም ለብቻቸው መግለጫ አውጥተዋል፡፡ ይህ “የሚያጸጽትና ተቀባይነት የሌለው ነው” ነው ሶማሊያ ያለችው፡፡
በኮሚሽኑ የፖለቲካ፣ የጸጥታ እና ደህንነት ጉዳዮች የወጣውን መግለጫ እንደማትቀበልም አስታውቃለች፡፡