ባሳለፍነው ወር በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል ከወትሮው በተለየ የመደበትና የመጨነቅ ሁኔታዎች ተስተውለዋል ተብሏል
በአማራ ክልል ከወትሮው ከፍ ያለ የመደበትና የመጨነቅ ችግር መስተዋሉን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ
ባሳለፍነው ወር በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል ከወትሮው በተለየ የመደበትና የመጨነቅ ሁኔታዎች መስተዋላቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡
በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት የአዕምሮ ህመም ተጠቂዎች ቁጥር ከፍ እያለ መምጣቱን የገለጹት የድርጅቱ የአዕምሮ ጤና ዳይሬክተር ዲቮራ ኬስቴል ይኸው ጉዳይ ከፍ ባለ ሁኔታ ባሳለፍነው ወር በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡
በክልሉ ይስተዋል የነበረው የመጨነቅና የመደበት ችግር ወረርሽኙ ከመከሰቱ አስቀድሞ ከነበረበት በሶስት እጥፍ ከፍ ብሎ የተጋላጭነት ምጣኔው ወደ 33 በመቶ ከፍ ብሏል እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ፡፡
በወረርሽኙ ሳቢያ የሚያጋጥመው ሞት፣ተለይቶ መቆየት፣ፍርሃት እና ጭንቀት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የአዕምሮ ህመም ተጠቂዎች ቁጥር ከፍ ሊያደርገው እንደሚችልም ዶ/ር ኬስቴል ከሚመሩት ተቋም የሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
በመሆኑም መንግስታት የዜጎቻቸውን የአዕምሮ ጤና ለመጠበቅ ከወረርሽኙ ጎን ለጎን ቅድሚያ ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ዳይሬክተሯ አሳስበዋል፡፡
ኮሮና ቫይረስ እስካሁን በአማራ ክልል 4 ዞኖች ተከስቷል፡፡ አስፈላጊው ምርመራ ከተደረገላቸው 565 ሰዎች መካከል 9ኙ በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡንም ከክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡