ዋሽንግተን ማዕቀብ የኢራን ኬሚካሎችን በመግዛት ወደ ውጭ ልከዋል የተባሉ ኩባንያዎች ላይ ያነጣጠረ ነው
ዩናይትድ ስቴትስ ለኢራን ሽያጮች በሚያመቻቹ ተዋናዮች ላይ ማዕቀብ መጣሌን እቀጥላሉ ብላለች።
ዋሽንግተን የኢራን ፔትሮ ኬሚካል እና የነዳጅ ምርቶች በምስራቅ እስያ ላሉ ገዥዎች እንዲሸጡ አመቻችተዋል ባለቻቸው በቻይና፣ ሆንግ ኮንግ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች የሚገኙ ከደርዘን በላይ ኩባንያዎች ላይ ማዕቀብ ጥላለች።
የኢራን የእ.አ.አ 2015 የኒውክሌር ስምምነት ለማደስ የተደረገው ጥረት በመቋረጡ እና ኢራናውያን መንግስታዊ ተቃውሞ መቀጠል በሀገሪቱ እና በምዕራቡ ዓለም መካከል ያለው ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዲሻክር አድርጓል ተብላል።
የኢራን ኬሚካሎችን ወደ ውጭ በመላክ ረገድ ዋሽንግተን የቻይና ኩባንያዎችን ኢላማ ያደረገች ሲሆን፤ የኒውክሌር ውልን የማደስ ተስፋም እየጨለመ መጥቷል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
የአሜሪካ ግምጃ ቤት ባወጣው መግለጫ የኢራን ፔትሮ ኬሚካል እና የነዳጅ ምርቶች በምስራቅ እስያ ላሉ ገዥዎች ማዕቀብ የተጣለባቸውን ኩባንያዎች በመወከል ሽያጭ አመቻችተዋል ባላቸው 3 ኩባንያዎች ላይ ነው እርምጃውን የወሰደው።
ሽያጩም በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ነው ተብሏል
የግምጃ ቤቱ የሽብር እና የፋይናንስ ደህንነት ምክትል ጸሀፊ ብሪያን ኔልሰን “ዩናይትድ ስቴትስ እነዚህን ሽያጮች በሚያመቻቹ ተዋናዮች ላይ ማዕቀብ መተግበሯን ትቀጥላለች” ብለዋል።
በማዕቀቡ መሰረት ኩባንያዎቹ ማንኛውንም የአሜሪካ ንብረቶች እንዳያንቀሳቅሱ እግድ ተጥሎባቸዋል። በአጠቃላይም አሜሪካውያን ከኩባንያዎቹ ጋር እንዳይገናኙ ማዕቀቡ ይከለክላል ነው የተባለው።
ከዚህ ባለፈም ከኩባንያዎቹ ጋር በተወሰኑ ግብይቶች ውስጥ የሚሳተፉትም በእገዳ የመመታታት ስጋት አለባቸው ተብሏል።