የኤምሬትስ የሃይል ምንጭ የማስፋት ትልም
በነዳጅ ሀብት ክምችቷ ከአለም ሰባተኛ ደረጃ የተቀመጠችው አረብ ኤምሬትስ የሃይል ፍጆታዋን በታዳሽ አማራጭ ለመተካት እየተጋች ነው
ሀገሪቱ በ2050 ከካርበን ብክለት የጸዳች ሀገር ለመሆን ስትራቴጂ ነድፋ በመስራት ላይ ትገኛለች
ኤምሬትስ ከብክለት የጸዳና ከነዳጅ ጥገኝነት የተላቀቀ ኢኮኖሚ በመገንባት ላይ ትገኛለች።
ሀገሪቱ በነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሃብት ክምችቷ ከቀዳሚዎቹ ሀገራት ብትመደብም ታዳሽ የሃይል አማራጭ ላይ በስፋት መስራትን መርጣለች።
ማስዳር የተሰኘው ግዙፍ ኩባንያዋም በጸሃይ፣ በንፋስ እና ሌሎች ታዳሽ የሃይል ማመንጫዎች ከኤምሬትስ አልፎ አለማቀፍ ተጽዕኖ በመፍጠር ላይ ይገኛል።
ሶስት በአለማቀፍ ደረጃ ግዙፍ የጸሃይ ሃይል ማመንጫዎች ያሏት አቡዳቢ፥ በሶስት የኒዩክሌር ማብለያዎችም ከብክለት የጸዳ የኤሌክትሪክ ሃይል ታመነጫለች።
ከኢንዱስትሪዎች የሚወጣ ካርበን ከባቢ አየርን ሳይበክል ይዞ የሚያስቀር ቴክኖሎጂ በመጠቀምም በመካከለኛው ምስራቅ ቀዳሚዋ ሀገር ናት።
ኤምሬትስ በ2050 ከጠቅላላ የሃይል ፍጆታዋ የታዳሽ ሃይል ድርሻ ምን መምሰል እንዳለበት የያዘችውን እቅድ በቀጣዩ ገላጭ ምስል ይመልከቱ፦