አረብ ኢምሬትስ ለሶሪያ 430 ቶን ሰብአዊ እርዳታ ላከች
አረብ ኢምሬትስ ምግብ፣ መድሃኒትና መጠለያ ድንኳኖች ለሶሪያ ርእደ መሬት ተጎጂዎች ልካለች
በሶሪያ በተከሰተ ርዕደ መሬት ከ3 ሺህ በላይ ሰዎች መሞታቸው ይታወቃል
የተባበሩት አረብ እምሬትስ በሶሪያ በመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎዱ ሰዎች የሰብአዊ እርዳታ መላኳን አስታወች።
አረብ ኢምሬትስ ከአምስት ቀናት በፊት በርዕደ መሬት ለተመቱት ቱርክ እና ሶሪያ ድጋፍ ማደረግ መቀጠሏን የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ በዛሬው እለት እንዳስታወቀው፤ ወደ ሶሪያ ደማስቆ በርካታ ካርጎ አውሮፕላን በረራዎችን በማድረግ 430 ቶን ሰብአዊ እርዳታ ማድረስ ተችሏል።
ለሶሪያ ከተላኩት የእርዳታ ቁሳቁስ መካከልም 20 ቶን መድሃትና የህክምና ቁሳቁስ፣ 155 ቶ ምግብ ነክ ቁሳቁሶች እንዲሁም 2 ሺህ 58 መጠለያ ድንኳኖችን ወደ ሶሪያ ምደረስ ማቸሉን የአረብ ኢምሬትስ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የአረብ ኢሚሬስት ፕሬዚዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን፤ በቱርክ እና በሶሪያ ያጋጠመውን ርእደ መሬት ተከትሎ ድጋፍ የሚያደርግ የኦፕሬሽን ኮማንድ እንዲቋቋም ማዘዛቸው ይታወሳል።
ይህንን ተከትሎም የተቋቋመው ኮማድ በሶሪያ እና በቱርክ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ለተጎዱ ሰዎች እርዳታ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ።
በደቡባዊ ቱርክ እና ሰሜናዊ ቱርክ እንዲሁም በሶሪያ ከአምስት ቀናት በፊት ባጋጠመ ከባድ ርዕደ መሬት አደጋ የሟቾች ቁጥር በየዕለቱ በማሻቀብ ላይ ይገኛል።
በቱርክ ብቻ እስከ ዛሬ ድረስ የሟቾች ቁጥር ከ21 ሺህ በላይ የተደረሰ ሲሆን፤ በሶሪያም ከ3 ሺህ በሉ ሰዎች ሞተዋል፤ በድምሩም እስካሁን የሞቱ ሰዎች ቁጥር 25 ሺህ ገደማ ደርሷል።
ይህ አደጋም በመሰረተ ልማት ላይ ባደረሰው ጉዳት ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኪሳራ እንደሚያደርስ ተተንብዩዋል።