አረብ ኢምሬት በአንድ ቀን ውስጥ 117 ቶን ምግብ ወደ ቱርክ እና ሶሪያ ላከች
በቱርክ እና ሶሪያ በደረሰ የርዕደ መሬት አደጋ የሟቾች ቁጥር ከ25 ሺህ አልፏል
የዓለም ሀገራት ሁሉ አደጋው ለደረሰባቸው ሁለቱ ሀገራት ተጎጂዎች ድጋፍ በማድረግ ላይ ናቸው
አረብ ኢምሬት በአንድ ቀን ውስጥ 117 ቶን ምግብ ወደ ቱርክ እና ሶሪያ ላከች።
የተባበሩት አረብ ኢምሬት ከአምስት ቀናት በፊት በርዕደ መሬት ለተመቱት ቱርክ እና ሶሪያ ድጋፍ በማድረግ ላይ ትገኛለች።
በዛሬው ዕለትም በአንድ ቀን ውስጥ 117 ቶን ህይወት አድን ድጋፎችን ወደ ሁለቱ ሀገራት ልካለች።
የአረብ ኢምሬት ድጋፍ አገልግሎት ተቋም ከበጎ ፈቃደኞች ጋር በመተባበር በአደጋው ክፉኛ ለተጎዱት ቱርክ እና ሶሪያ ድጋፍ ማድረጉ እንደሚቀጥልም ተገልጿል።
በደቡባዊ ቱርክ እና ሰሜናዊ ቱርክ ከአምስት ቀናት በፊት ባጋጠመ ከባድ ርዕደ መሬት አደጋ የሟቾች ቁጥር በየዕለቱ በማሻቀብ ላይ ይገኛል።
በቱርክ ብቻ እስከ ዛሬ ድረስ የሟቾች ቁጥር ከ21 ሺህ በላይ ደርሷል።
ይህ አደጋም በመሰረተ ልማት ላይ ባደረሰው ጉዳት ከ4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኪሳራ እንደሚያደርስ ተተንብዩዋል።