አረብ ኤምሬትስ በአለምአቀፍ ተወዳዳሪነት መመዘኛ ከቀዳሚ 5 ሀገራት ውስጥ ተካተተች
በዚህ ሪፖርት 67 ሀገራት የተሸፈኑ ሲሆን አለምአቀፋዊ የሀገራት ተወዳዳሪነት ማጣቃሻ ሆኖ ይጠቀሳል።
አመታዊው አለምአቀፍ የተወዳዳሪነት መመዘኛ ሪፖርት የሚሸፍናቸውን ሀገራት በአራት ዋና እና በ20 ንዑስ ዘርፎች ይከፍላል
አረብ ኤምሬትስ አለምአቀፍ ተወዳዳሪነት መመዘኛ ከቀዳሚ 5 ሀገራት ውስጥ ተካተተች።
ኤምሬትስ በመንግስት የአፈጻጸም ብቃት በ2024ቱ 'የግሎባል ኮምፒቴቲቭነስ ኢንዴክስ' ወይም በዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት መመዘኛ ከቀዳሚ አምስት ሀገራት ውስጥ መካተት ችላለች።
አመታዊው አለምአቀፍ የተወዳዳሪነት መመዘኛ ሪፖርት የሚሸፍናቸውን ሀገራት በአራት ዋና እና በ20 ንዑስ የሚከፍል ሲሆን በአስተዳደር፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ መስኮች 336 ማወዳደሪያ ነጥቦችን ይጠቀማል።
በዚህ መሰረት አረብ ኢምሬትስ በአለምአቀፍ አመራርነት ተመዝና ከ90 በላይ በሚሆኑት የተወዳዳሪነት መለኪያዎች አዎንታዊ ውጤት አስመዝግባለች።
በሪፖርቱ መሰረት በአለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ቀዳሚ የሆኑት አምስት ሀገራት የሚከተሉት ናቸው።
1-ስዊዘርላንድ
2-ሲንጋፖር
3-ሆንግ ኮኖግ
4-አረብ ኢምሬትስ
5-ዴንማርክ
አመታዊ የአለምአቀፍ ተወዳዳሪ ሪፖርት ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመው በፈረንጆቹ 1928 ሲሆን የታተመውም ዋና መቀመጫውን ሉዋዛኔ ስዊዘርላንድ ባደረገው የአለምአቀፍ ተወዳዳሪነት ማዕቀል ነው።
ሪፖርቱ ደረጃዎችን ለማስቀመጥ የንግድ ማህበረሰብ አስተያየት እና 2/3ኛውን ደግሞ ከስታቲስቲክስ በሚያገኘው ተመርኩዞ ነው ተብሏል።
በዚህ ሪፖርት 67 ሀገራት የተሸፈኑ ሲሆን አለምአቀፋዊ የሀገራት ተወዳዳሪነት ማጣቃሻ ሆኖ ይጠቀሳል። ሪፓርቱ ሀገራት በኢኮኖሚ፣ በመንግስት አስተዳደር፣ በንግድ እና በመሰረተልማት ዘርፎች ያላቸውን አቅም ከግምት ያስገባል።