አረብ ኢምሬትስ ከ ''ኤፍ.ኤ.ቲ.ኤ'' ግራጫ ዝርዝር ውስጥ እንድትወጣ ተደርገ፤ ይህ ምን ማለት ነው?
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስን ወደ አርአያነት የሚለውጥ እርጃ ነው
አረብ ኢሚሬትስ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርንና የአሸባሪዎችን የገንዘብ ድጋፍ ወንጀሎችን በመዋጋት ስኬት አስመዝግለች
አረብ ኢምሬትስ በዓለም አቀፍ የፋይናንስ የተግባር ግብረ ሃይል ፀረ-ገንዘብ ማሸሽ ''ኤፍ.ኤ.ቲ.ኤ'' ግራጫ ዝርዝር ውስጥ እንድትወጣ ተደርገ።
በዓለም አቀፍ የፋይናንስ የተግባር ግብረ ሃይል ፀረ-ገንዘብ ማሸሽ ዛሬ በፓሪስ ባካሄደው አጠቃላይ ስብሰባው መጨረሻ ላይ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ከ"ግራጫ መዝገብ" እንድትወገድ ያሳለፈውን ውሳኔ አጽድቆታል።
የኤሚሬትስን ስም ከግራጫ ዝርዝር ውስጥ መውጣቷ የሀገሪቱ መንግስት ባደረገው ያልተቋረጠ ጥረት እና ማሻሻያ ላይ አለማቀፋዊ እምነት እያደገ መምጣቱን ያሳያል።
ፓሪስ ውስጥ ያለው የፋይናንሺያል ተግባር ግብረ ኃይል (FATF) "ግራጫ ዝርዝር" ምንድን ነው? የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ከዚህ ዝርዝር መውጣቷ ምን ማለት ነው?
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ኢኮኖሚ በአገር ውስጥ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ምን ጥቅሞች አሉት?
የ ''ኤፍ.ኤ.ቲ.ኤ'' ግራጫ ዝርዝር ምንድነው?
የአረብ ኢምሬትስ ህገ ወጥ ገንዘብ ዝውውር፣ ሽብርተኝነትን በገንዘብ መደገፍ እና ህገ ወጥ ድርጅቶችን በገንዘብ መደገፍን የሚከላል ብሄራዊ ኮሚቴ በድረ ገጹ ላይ ባወጣው መግለጫ፤ የፋይናንስ የተግባር ግብረ ሃይል በህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውርን መከላከል ውስጥ ውስጥ ያሉ ስልታዊ ድክመቶችን ለመፍታት የተጠናከረ ክትትል የሚያደርግ ነው።
ኤፍ.ኤ.ቲ.ኤ አንድን ሀገር በተጠናከረ ክትትል ውስጥ ሲያስገባ፣ በገሪቱ በተቀመጠላት የጊዜ ገደብ ውስጥ የታዩ ስትራቴጂያዊ ድክመቶችን በፍጥነት ለመፍታት ቁርጠኛ ነች ማለት ነው። በዚህ ምድብ ውስጥ ከፍተኛ ክትትል የሚደረግባቸው ሀገራን የያዘው ዝርዝር "ግራጫ (ግሬይ) ዝርዝር" ይባላል።
የኤፍ.ኤ.ቲ.ኤፍ ድረ-ገጽ እንዳስነበበው የፋይናንሺያል አክሽን ግብረ ሃይል ከግራጫ ዝርዝር ውስጥ ካሉ ሀገራት ጋር በመሆን የስትራቴጂክ ጉድለቶቻቸውን ለመፍታት የተደረገውን ለውጥ ሪፖርት ለማቅረብ መስራታቸውን ቀጥለዋል።
እስካሁን ድረስ የሚከተሉት 23 ሀገራት ሕገወጥ የገንዘብ ፍሰትን ለመዋጋት እድገትን ለመገምገም በኤፍ.ኤ.ቲ.ኤፍ ግራጫ ዝርዝር ውስጥ ይገኛሉ የተባለ ሲሆን፤ ሀገራም ባርባዶስ፣ ቡልጋሪያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ካሜሩን፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ክሮኤሺያ፣ ጊብራልታር፣ ሄይቲ፣ ጃማይካ፣ ማሊ፣ ሞዛምቢክ፣ ናይጄሪያ ፊሊፒንስ፣ ሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ሶሪያ፣ ቱርክ፣ ኢሚሬትስ፣ ቬትናም እና የመን ናው ብሏል ተቋሙ በድረ ገጹ።
የፋይናንሺያል አክሽን ግብረ ሃይል (ኤፍ.ኤ.ቲ.ኤፍ) ዮርዳኖስን፣ ፓናማን፣ አልባኒያን እና የካይማን ደሴቶችን ከግራጫ ዝርዝር ውስጥ በጥቅምት 2023 ማስወጣቱም ተነግሯል።
የፋይናንሺያል አክሽን ግብረ ሃይል (ኤፍ.ኤ.ቲ.ኤፍ) ሃይል ፀረ-ገንዘብ ማሸሽ ዛሬ በፓሪስ ባካሄደው አጠቃላይ ስብሰባው መጨረሻ ላይ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ከ"ግራጫ መዝገብ" እንድትወገድ ያሳለፈውን ውሳኔ አጽድቋል።
አረብ ኢሚሬትስ ከኤፍ.ኤ.ቲ.ኤፍ ግራጫ ዝርዝር መውጣት ምን ማለት ነው?