የአረብ ኢሚሬትስ ቆሰሉ ፍሊስጤማውያን ህጻትን ከጋዛ መቀበል ጀመረች
የአረብ ኢምሬት ፕሬዝዳንት የመንግስት ሆስፒታሎች ፍልስጤማዊያን ህጻናት እንዲጠለሉባቸው መወሰናቸው ይታወሳል
የአረብ ኢምሬትስ ነብስ አድን ቡድን በራፋ ድንበር በኩል ተጎጂዎችን መቀበል ጀምረዋል
የአረብ ኢሚሬትስ ቆሰሉ ፍሊስጤማውያን ከጋዛ በማስተጣት ወደ ሀገሯ የማጓጓ ስራ ዛሬ በይፋ ጀመረች።
የተባበሩት አረብ ኢምሬት የመንግስት ሆስፒታሎች አንድ ሺህ ፍልስጤማዊያን ህጻናት እና ቤተሰቦቻቸው እንዲስተናገዱባቸው መወሰኗ ይታወሳል።
- በጋዛ የሚገኙ የተጎጂ ቤተሰቦች ለተደረገላቸው ድጋፍ አረብ ኢምሬትስን አመሰገኑ
- የአረብ ኢምሬት ፕሬዝዳንት የመንግስት ሆስፒታሎች ፍልስጤማዊያን ህጻናት እንዲጠለሉባቸው ወሰኑ
የአረብ ኢምሬት ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን የመንግስት ሆስፒታሎች ፍልስጤማዊያን እንዲስተናገዱባቸው ከቀናት በፊት ወስነዋል።
ይህንን ተከትሎም የአረብ ኢምሬትስ ነብስ አድን ቡድን በግብጽና በጋዛ መካከል በሚገኘው በራፋ ድንበር በኩል ተጎጂዎችን መቀበል ጀምረዋል።
ተጎጂዎችን ከግብጽ አል አርሽ አውሮፕላን ማረፊያ ወደ አረብ ኢሚሬትስ በአውሮፕላን ለማጓጓዝ ዝግጅት እየተደረገም ይገገኛል።
በዛሬው እለት አመሻሽ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጋዛ ጦርነት ተጎጂዎች በራፋ ድንበር በኩል ወደ ግብጽ ተሸግረው ምጋባታቸው ታውቋል።
የግብጽ አምቡላንሶችም ተጎጂዎችን ሙሉ በሙሉ ከጋዛ ሰርጥ ወደ ግብጽ ሲገቡ ወደ አል አሪሽ አውሮፕለን ማረፊያ ለማጓጓዝ በተጠንቀው ላይ መሆናቸውም ነው የተነገረው።
የአረብ ኢምሬት ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን የመንግስት ሆስፒታሎች ፍልስጤማዊያን እንዲስተናገዱባቸው መወሰናቸው ይታወሳል።
ሀገሪቱ ፍልስጤማዊያን ህጻናት እና ቤተሰቦቻቸው በመንግስት ሆስፒታል የህክምና እና ሌሎች መሰረታዊ ድጋፎች ይደረግላቸዋልም ተብሏል።