ዩኤኢ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ወጥረት መርገብ አለበት አለች
ኤሜሪካ በኢራቅ ውሰጥ የኢራንን ጄነራል ቃሲም ሱሌማኒን ከገደለች በኋላ ኢራን የበቀል እርምጃ መወሰድ መጀመሯን ተከትሎ በመካከለኛ ምስራቅ ያለው ውጥረት አይሎ ቀጥሏል፡፡
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (ዩኤኢ) ውጥረቱ እንደሚሳስባትና ፖለቲካዊ መፍትሄ እንደሚያስፈልገው ገልጻለች፡፡
የዩኤኢ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አንዋር ቢን ሞሀመድ ጋርጋሽ በመካካለኛው ምስራቅ ያለውን ሁኔታ ማረጋጋትና ውጥረቱን ማርገብ አስፋለጊ ስለሆነ፣ አስቸኳይ የመፍትሄ እርምጃ ሊወሰድ ይገባል ብለዋል፡፡
የቀጠናው ፖለቲካ ተለዋዋጭ ስለሆነ፣ ቀጠናውን ለማረጋጋት ፈጣን ፖለቲካዊ መፍትሄ እንደሚያሻም ሚኒስትር ዴኤታው በትዊተር ገጻቸው ጠቅሰዋል፡፡
ሚንስትር ዴኤታው ዉጥረትና መፋጠጥን ለማርገብ ጥበብ፣ ሚዛናዊነትንና ፖለቲካው መፍትሄን መጠቀም እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል፡፡
የበቀል እርምጃ ነው በተባለው ጥቃት፣ ኢራን በኢራቅ በሚገኘው የአሜሪካ የጦር ሰፈር ላይ ከደርዘን በላይ ሜሳኤል ማስወንጨፏን የአሜሪካ መከላከያ ፔንታጎን አስታውቋል፡፡