“የአብርሃም የሰላም ስምምነት“ ለመካከለኛው ምስራቅ አዲስ ራዕይ ነው በዋሺንግተን የዩኤኢ አምባሳደር
ዩኤኢ ለቀጣናው እና ለዓለም ሰላምና ብልጽግና የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል የሱፍ አል-ኡተይባ ተናግረዋል
“የአረብ ህዝብ ግጭት ሰልችቶታል” ሲሉ አምባሳደር የሱፍ አል-ኡተይባ ለአል ዐይን ገልጸዋል
“የአብርሃም የሰላም ስምምነት“ ለመካከለኛው ምስራቅ አዲስ ራዕይ ነው በዋሺንግተን የዩኤኢ አምባሳደር
በዋሺንግተን የኤምሬትስ አምባሳደር የሆኑት የሱፍ አል-ኡተይባ ለ 12 ዓመት ያህል በአሜሪካ ዋሺንግተን ያገለገሉና በርካታ ዓለም አቀፍ ወሳኝ ሁነቶች ላይ የተሳተፉ ሲሆን ፣ አምባሳደሩ ከታላላቅ ዲፕሎማቶች አንዱ ብቻ ሳይሆኑ በ 2020 ከታይም መጽሔት 100 ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው፡፡
በእስራኤል ጋዜጣ “የዲኦት አህሮኖት” ያሳተሙት መጣጥፋቸው በቴል አቪቭ እና አቡ ዳቢ መካከል ለተጀመረው የሰላም አቅጣጫ ፈር ቀዳጅ ነበር፡፡ በመቀጠልም በእስራኤል እና በኤምሬትስ የሰላም ስምምነት የስኬቱን አክሊል ባለፈው መስከረም ወር በኋይት ሀውስ ደፍተዋል፡፡
አል አይን ኒውስ ከአንጋፋው የኤምሬትስ ዲፕሎማት ጋር ቆይታ አድርጓል፡፡
አል አይን ኒውስ አንጋፋውን የኤምሬትስ ዲፕሎማት በአሜሪካ ዋሽንግተን አግኝቶ አነጋግሯል፡፡ በውይይታችንም ከእስራኤል ጋር የነበረው የሰላም ስምምነት ሂደት እንዲሁም የፍልስጤምን ጥቅሞች ከማስጠበቅ አንጻር የሁለትዮሽ ድርድሩ ምን ይመስል እንደነበር አስረድተዋል፡፡ የአል ዐይን ጥያቄዎች እና የእርሳቸው ምላሽ እንደሚከተለው ቀርበዋል ፤ መልካም ንባብ!
● እኛ ዛሬ የምንኖረው በቀጣናው እና በአረብ-እስራኤል ግንኙነት ታሪክ በልዩ ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡ ክቡር አምባሳደር በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና በእስራኤል መንግስት መካከል የተፈጠረውን የሰላም ስምምነት ውልደት ፣ ታሪክ እና ስሙ “የአብርሀም ስምምነት” ተብሎ ስለሚጠራበት ምክንያት ለብዙሀኑ ሊገልጹልን ይችላሉ? ብዙዎች እርስዎ ከዚህ የሰላም ስምምነት ንድፍ አውጪዎች አንዱ እንደሆኑ ይገልጹዎታል?
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የፍልስጤምን ህዝብ ከመደገፍ እንዲሁም በየደረጃው ለሀገሪቱ ጉዳዮች ከምታደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አንድም ቀን ወደ ኋላ ብላ አታውቅም፡፡ ይህም በውጭ ፖሊሲያችን ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች መካከል ነው፡፡ ሆኖም ግን የፍልስጤምን መንግስት መመስረትን በተመለከተ ባለፉት ዓመታት ምንም ተጨባጭ እድገት አልታየም፡፡ እስራኤል አዲስ የፍልስጤም ምድርን ለማካተት እና በመሬት ላይ አዲስ እውነታ የመፍጠር ውጥን ቢኖራትም ፣ ዩኤኢ ፍልስጤምን የማካተት ሀሳብ አደገኛ መሆኑን ለእስራኤላውያን ከማስረጽ አንጻር ተሳክቶላታል፡፡ የማካተት እቅድ ከአረቡ ዓለም ጋር በደህንነት ፣ በኢኮኖሚ እና በባህላዊ ዘርፎች ግንኙነቶችን የማሻሻል ፍላጎቶችን የሚጎዳ ነው፡፡ በእውነቱ በሀገሪቱ ብልህ አመራሮች ድጋፍ በእብራይስጥ ቋንቋ አንድ ጽሑፍ የእስራኤል “የዲኦት አህሮኖት” ጋዜጣ ላይ በርእሰ አንቀጽ መልክ ጽፌ ነበር፡፡
በእርግጥ ጽሑፉ በእስራኤል መንግሥት ፣ በሁሉም የፖለቲከኛውም በህዝብም ደረጃ ሰፊ መስተጋብርን ያገኘ ሲሆን ፣ የፍልስጤምን መሬቶችን ለማካተት ያቀደውን የእስራኤል ውጥን የማይቀበሉት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፣ ሌሎች የአረብ እና የአውሮፓ ሀገራትን አቋምም የደገፈ ነበር፡፡
ከዚያ መጣጥፉ በኋይት ሀውስ ድጋፍ ዲፕሎማሲያዊ የውይይት ማዕበል እንዲነሳ ያደረገ ሲሆን ፣ የአብርሃም የሰላም ስምምነት እንደታወጅ ምክንያት ሆኗል፡፡
“የአብርሃም ስምምነት” የሚለው የስምምነቱ ስያሜ ፣ ለሦስቱ ሃይማኖቶች ተምሳሌታዊ እሳቤዎችን ለመግለጽ ታስቦ ነው የተመረጠው ፡፡
● በእርስዎ አስተያየት በቅርቡ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና በእስራኤል መካከል ከተደረገው ስምምነት በስተጀርባ በአጠቃላይ ቀጣናው ሊያተርፋቸው ከሚችላቸው ጠቀሜታዎች መካከል ቢጠቅሱልን?
በእርግጥ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፖሊሲ በሚዛናዊነትና ፍትሀዊነት ላይ እንዲሁም በወንድም ና በወዳጅ ሀገሮች መካከል ውይይትና መግባባትን ለመፍጠር በሚያስችሉ መሠረቶች ላይ የተመሠረተ ነው፡፡
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችም ዓለም አቀፍ አለመግባባቶችን በውይይት እና በዲፕሎማሲያዊ መንገዶች ለመፍታት እንዲሁም ለዓለም አቀፍ ሰላምና ፀጥታ መጠናከር የበኩሏን አስተዋፅኦ እንዳደረገች በግልጽ አሳይታለች፡፡ በዚህም በአረብ ሀገራትና በእስራኤል መንግስት መካከል ባለው የሰላም እውነታ እርካታ አልነበራትም ፡፡
ይበልጥ ግልጽ አድርጎ ለመናገር ያህል የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች በቀጣናው ውስጥ ቀጣይ ትውልዶች የሚደሰቱበትን እውነተኛ አዎንታዊ ለውጥ የሚያመጣ ጠንካራ ሰላም ትፈልጋለች፡፡ አንዳንድ ልዩነቶች ወደ ተሻለ የወደፊት ሕይወት የሚወስዱ ግንኙነቶችን እና ውይይቶችን ከመመስረት ሊያግዱን አይገባም፡፡
በአጠቃላይ ቀጣናውን ሊጠቅሙ የሚችሉ ትሩፋቶችን አስመልክቶ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና በእስራኤል መንግስት መካከል በጋራ ትብብር ላይ የተመሰረቱ ፈር ቀዳጅ ፕሮጀክቶች የተጀመሩት በፈረንጆች ነሐሴ 13 የአብርሃም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ እንደሆነ ሁሉም ያውቃል፡፡
እ.ኤ.አ መስከረም 15 በዋሺንግተን የአብርሃም ስምምነት ከተፈረመ በኋላ ደግሞ ለኮሮና ወረርሽኝ (ኮቪድ-19) መፍትሄ ለማምጣት በበርካታ የሚመለከታቸው አካላት ፣ በተለይም በግሉ ሴክተር እና በሁለቱ ሀገራት የምርምር ማዕከላት መካከል ስምምነት ተደርሷል፡፡ የንግድ ዘርፍ መሪዎችም እርስ በእርስ መወያየት የጀመሩ ሲሆን ፣ በቴክኖሎጂ መስኮች የተሰማሩ ስፔሻሊስቶች እንዲገናኙ እና የሁለቱ ሀገራት ቱሪስቶችም አንዳቸው በሌላኛቸው ሀገር የእረፍት ጊዜያቸውን ለማሳለፍ ማቀድ ጀምረዋል፡፡ ይህ ጅምር ነው ፤ እናም ይህን ታሪካዊ ስምምነት ተከትሎ ፣ እነዚህን የመሳሰሉ ከፍተኛ ጥቅማጥቅሞችን የሚያገኙት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና እስራኤል ብቻ ሳይሆኑ ቀጣናው እና በአጠቃላይ የዓለም ሀገራት ናቸው፡፡
የአብርሃም ስምምነት አንዱ ፍሬ ነገር በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ፣ በእስራኤል እና በአሜሪካ የተቋቋመው የ 3 ቢሊዮን ዶላር የአብርሃምክ ፈንድ ነው፡፡ ይህም በአከባቢውና በመካከለኛው ምስራቅ ኢኮኖሚያዊ ትብብር እና ብልጽግናን ለማሳደግ በግሉ ዘርፍ የሚመሩትን የኢንቬስትመንት እና የልማት እቅዶች ለመደገፍ የሚውል ነው፡፡ ይህ ደግሞ የቀጣናውን ንግድ ከፍ የሚያደርግ ፣ ስትራቴጂካዊ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን የሚያነቃቃ እና አስተማማኝ እና ተመጣጣኝ የኤሌክትሪክ አቅርቦት በማስገኘት የኃይል አቅርቦትን የሚያሳድግ ነው፡፡ ስምምነቱ ቀጣናውን እንዴት እንደሚያሳድገው ይህ አንዱ ማሳያ ነው፡፡
● የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች የሰላም ተነሳሽነት የቀጣናውን ሰላም አንግቦ የመጣውን ባቡር ወደፊት በመግፋት ፣ የባህሬን መንግሥት እና የሱዳን ሪፐብሊክ እንዲቀላቀሉ በሩን ከፍቷል፡፡ ስለዚህ በእርስዎ ግምትና ልምድ በመቀጠል የሰላም ባቡርን የሚቀላቀሉ ሀገሮች እነማን ናቸው?
በእውነቱ ከሆነ ሌሎች ሀገሮች ምን ማድረግ እንዳለባቸው መናገር አልችልም ፤ ነገር ግን መካከለኛው ምስራቅ በፍጥነት ሰላምን ለማስፋት ተጨማሪ ትብብር እና ድፍረት የተሞላበት እርምጃ እንደሚፈልግ አጥብቄ እገልጻለሁ፡፡በአሁኑ ሰአት ቀጠናው ከባድ የኢኮኖሚ ፣ የፖለቲካ ፣ የአካባቢ እና የፀጥታ ችግሮች እየገጠሙት ሲሆን እነዚህ ሁሉ ከፍተኛ ትብብር እና ቅንጅት ይፈልጋሉ ፡፡ የአረብ ህዝብ ግጭት ስለሰለቸው ፣ የተረጋጋ እና የበለፀገ ቀጣና ውስጥ ለመኖር የሚናፍቅ በመሆኑ የአብርሃም የሰላም ስምምነት ወደ አዲስ ፣ ተፈፃሚ ራዕይ የሚያሸጋግር ነው፡፡ የተለያዩ አካሄዶችን ለማስተዋወቅ እና ለቀጣናው የወደፊት እጣ ፈንታ አዲስ እና የተሻለ መንገድን ለማመላከት ጊዜው አሁን ነው ፡፡
● እንደጠቀሱት የፍልስጤምን ጉዳይ መደገፍ በኤምሬትስ የውጭ ፖሊሲ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ወሳኝ ጉዳዮች አካል ነው፡፡ ይህም ሆኖ አንዳንዶች በሰሞኑ የሰላም ስምምነት ላይ ጥያቄ ያነሳሉ ፡፡ .. ለሰላም ሂደት ተጠራጣሪዎች ወይም ተቺዎች የሚሰጡት ምላሽ ምንድነው?
በግልጽ ለመናገር ይህ ስምምነት ለሁሉም ሰው እንዲደርስ እንፈልጋለን፡፡ የፍልስጤም ህዝብም ነፃ ሆኖ በትውልድ ሀገሩ በሰላም ፣ በክብር እና በደህንነት መኖር ይገባዋል፡፡ ይህ ስምምነት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለፍልስጤም ህዝቦች ያላትን ቁርጠኝነትና ጥልቅ ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ ግንኙነትን የሚያጠናክር ሲሆን የሁለት ሀገራት መፍትሄ ግባችንን የሚያንፀባርቅ እና በአካባቢያችን ብልጽግናን የሚያረጋጋጥ ነው፡፡
የአብርሃም የሰላም ስምምነት የመካከለኛው ምስራቅ አካባቢን ሰላም ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ለማሳደግ ወሳኝ እርምጃ ነው፡፡ ስምምነቱ በፍልስጤም እና በእስራኤል መካከል ለወደፊቱ የሚደረገውን ድርድር ትርጉም ያለው እና ተስፋ ሰጭ የሚያደርግ መሆኑን በማመን ብሎም አዲስ የፍልስጤም መሬትን ለማካተት የሚደረገውን ጥረት የሚገታና የሁለት ሀገራት መፍትሄን የሰነቀ ነው፡፡
● ነገር ግን የአብርሃም የሰላም ስምምነትን መነሻ በማድረግ አንዳንድ የፍልስጤም ጉዳይ ነጋዴዎች ፣ በፍልስጤም ህዝብ እውነተኛ ፍላጎት ላይ ከጀርባው ተጠቃሚዎች እንደሆኑ ይገለጻል፡፡ የእርስዎ አስተያየት ምንድ ነው?
ይህንን ስምምነት የተፈራረምነው ለሰላም አዳዲስ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ሲሆን ሰፊ ዓለም አቀፍ ድጋፍም አግኝቷል፡፡ ስምምነቱ ለሁለቱን ሀገራት መፍትሄ የማምጣት እና ቀጠናዊ ብልጽግናና መረጋጋትን የማስፋት ግባችንን የሚያንፀባርቅ ሲሆን የዓለምአቀፍ ውሳኔዎች እና የአረብ የሰላም ኢኒሼቲቭን መሠረት ያደረገም ነው።የአብርሃም ስምምነት ለአካባቢው ሰላም ግንባታ ወሳኝ እርምጃ ነው፡፡
የማካተት እቅድን ማቆም በእኛ ፣ በእስራኤል እና በአሜሪካውያን መካከል የሶስትዮሽ ውይይቶች ከዋና ጥያቄዎች አንዱ ነበር፡፡ እናም የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ይህ ስኬት ፍልስጤም እና እስራኤል ትርጉም ወዳለው ድርድር እንዲመጡ ሊያደርግ ይችላል ብላ ታምናለች፡፡ ግን ግልጽ መሆን ያለበት ነገር ቢኖር ይህ ሰላማዊ መንገድ ወደፊት እንዲራመድ ኃላፊቱን የሚወስዱት ፍልስጤም እና እስራኤል ናቸው፡፡
● የአሁኑ የአሜሪካ ምርጫ በአሜሪካ ታሪክ ውስጥ በጣም ወሳኝ እንደሆነ ይገለጻል፡፡ በዚህ ጉዳይ የእርስዎ ምልከታ ምንድነው? ውጤቱስ በመካከለኛው ምስራቅ ሁኔታ እና በሰላም ሂደቱ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል ይላሉ?
የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ክቡር ሼህ አብደላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እ.ኤ.አ. በ 2021 ሀምሳኛ ዓመቷን ስታከብር ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት የመሰረተችበትንም 50ኛ ዓመት እንደምታከብር ሲጠቅሱ እንደ ነበር ማስታወስ ግድ ይላል። ሁለቱ ሀገራት በጋራ እሴቶች ላይ የተመሠረተ የወዳጅነት ግንኙነት አላቸው ፤ የተሻለ የወደፊት ጊዜ በጋራ እንዲኖራቸውም ይፈልጋሉ ፤ እናም ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ስልታዊ ግንኙነት ከምርጫ ሂደት እና ከፖለቲካ ፓርቲዎች የዘለለ ነው፡፡
ለማጠቃለል ያህል እኛ ፣ አሜሪካ በቀጣናው ንቁ ሚና ስትጫወት መካከለኛው ምስራቅ በተሻለ አቋም ላይ እንዲገኝ ይረዳል ብለን እናምናለን። እናም የምርጫው ውጤት ምንም ይሁን ምን እኛ ሁል ጊዜ ከአሜሪካ ጋር በጋራ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና ሰላምን ለማስፈን እንዲሁም አዎንታዊና ይበልጥ የበለፀገ ነገን ዕውን ለማድረግ ጥረት እናደርጋለን፡፡
● ቀደም ሲል ጠቅሰውታል ፤ በአሁኑ ጊዜ ያለው ዲፕሎማሲ በተለይም ከኮሮና ቫይረስ ቀውስ ጋር ተያያዞ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ አስፈላጊ ነው ፤ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን ዳግም አንድን መለከት የደረገ ይመስላል፡፡ በዚህ ላይ ምን ይላሉ?
በእርግጥ አሁን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ የዲፕሎማቲክ እርምጃ አስፈላጊነት እየታየ ነው የ “ኮቪድ -19” ወረርሽኝን የምናሸንፍበት ብቸኛው መንገድ በአለም ሀገሮች መካከል በመተባበር ነው፡፡ እኛ (የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች) የተከሰተውን ወረርሽኝ ለመቆጣጠር እና ስርጭቱን ለመግታት ዓለም አቀፍ ጥረቶችን ለመደገፍ ፣ ለሌሎች ሀገራት ዕርዳታ ለመስጠት ባደረግነው ስራ እጅግ ኩራት ይሰማናል፡፡ ያሳለፍናቸው ጊዜያት አንዳንድ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች መከለስ እንዳለባቸው አሳይቶናል፡፡ እናም ወረርሽኙ ፖሊሲዎቻችን እና የፖለቲካ አቋሞቻችንን የማይለውጥ ቢሆንም ሁሉንም በሰብአዊና የጋራ ትብብር መንገዶች ማሰብ እንዲቻል አነሳስቷል፡፡ ብሎም በአጠቃላይ የዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ዝግጁነትና በዓለም ላይ የሚገጥሙ ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ በተሳካ ሁኔታ ለማሸነፍ በጋራ ለመስራት የሚችል ማህበረሰብ መገንባት እንደሚገባም አሳይቷል፡፡
ይህንን ቀውስ እንደምን ሻገር ላረጋግጥልህ እወዳለሁ። ነገር ግን የወስድናቸው ትምህርቶች ለወደፊት ይጠቅሙናል።
ዓለም የአየር ንብረት ለውጥ እና ሌሎች ውስብስብ ችግሮችም ያጋጥሟታል፡፡ ከዚህ የወረርሽኝ ቀውስ በብቃት እንደምንሻገር እምነት አለኝ ፤ ከበፊቱ የበተሻለም በጣም ጠንካራ ነን፡፡
● ክቡር አምባሳደር ቀደም ሲል የአሜሪካ ታየም መጽሔት በ ‹2020› በዓለም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ካሳደሩ 100 ሰዎች መካከል አንዱ አድርጎ መርጠዎታል ፤ በዚህ ላይ አስተያየትዎ ምንድ ነው?
በእውነቱ ፣ በታይም መጽሔት አድናቆትን በማግኘቴና በተለይም የምወዳት ሀገሬ በመካከለኛው ምስራቅ የሰላም አዲስ ራዕይን ለመቅረጽ ላከናወነችው ስራ ክብር አለኝ፡፡ ግን በዚህ ዝርዝር ውስጥ መካተቴ ከሚገባኝ በላይ ሆኖብኛል ።
የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶችን ሚወክል ዲፕሎማት በመሆኔ እና መሪዎቻችን ያላቸውን አዎንታዊ የወደፊት ራዕይ ለማጠናከር በመስራቴ ታላቅ ክብር ይሰማኛል ፡፡ ይህ ዕውቅና እና አድናቆት በመካከለኛው ምስራቅ ለቀጣይ ውይይት ፣ ገንቢ የሆነ ተሳትፎ እና የሰላም ግንባታ ብሩህ ተምሳሌት ነው፡፡