ኢትዮጵያ በዱባይ ለሚካሄደው ኮፕ 28 በተለየ መልኩ ዝግጅት ማድረጓ ተገለጸ
በተጨባጭ መሬት ላይ እየተተገበሩ ያሉ ሥራዎችን ኢትዮጵያ በጉባዔው ላይ ታሳያለች
ኢትዮጵያ በ28ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ተሞክሮዎቿን እንደምታካፍልም አስታውቃለች
ኢትዮጵያ በተባበሩት አረብ ኢምሬተስ አስተናጋጅነረት በዱባጥ በሚካሄደው 28ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ በተለየ መልኩ ትልቅ ዝግጅት ማድረጓ ተገለጸ
የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ከህዳር 20 እስከ ታህሳስ 2 2016 ዓ.ም በሚካሄደው ኮፕ 28ና የኢትዮጵን ተሳትፎ አስምልከቶ መግለጫ ሰጥቷል።
በመግለጫውም ኢትዮጵያ በዱባይ በሚካሄደው 28ኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ኢትዮጵያ ተሞክሮዎቿን እንደምታካፍል ተገልጿል።
የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ነመራ ገበየሁ በመግለጫቸው የሚሆኑ ዝግጅቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ጉባዔው ከኅዳር 20 እስከ ታህሳስ 2 ቀን 2016 እንደሚካሄድና ከ130 በላይ አገራት በመሪዎች ደረጃ እንደሚሳተፉበት ጠቁመዋል።
በጉባዔው በተመረጡ ጉዳዮች ላይ ውይይቶች እንደሚደረጉ፣ አገራት አቋማቸውን እንደሚያሳውቁ እንዲሁም በሁለትዮሽ መድረኮች በርካታ ውይይቶች እንደሚካሄዱ ጠቁመዋል።
የድርድር መድረኮችም ሌላኛው የጉባዔው አካል መሆናቸውን ገልጸው፤ ይህም ትልቁን ቦታ የሚይዝ መሆኑን አመላክተዋል።
የፓሪሱ ስምምነት አፈጻጸም ግምገማ የጉባዔው ትልቅ አጀንዳ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ለውሳኔ ሰጪዎች መነሻ እንደሚሆን ይጠበቃል ብለዋል።
በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2015 ስምምነት የተደረሰበትን የፓሪሱን አጀንዳ ተፈጻሚ ከማድረግ አኳያ አገራት ምን እንዳከናወኑ በዚሁ መድረክ የሚዳሰስ መሆኑን ጠቁመዋል።
ከመደበኛው ውይይቶች ባሻገር ኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ የራሷን ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እንዲሁም በተጨባጭ መሬት ላይ እየተተገበሩ ያሉ ሥራዎችን የምታሳይበት መሆኑን አብራርተዋል።
በጉባዔው በርካታ ሥራዎችን ለመሥራት መታቀዱን እና ከዚህ ቀደም ከነበሩት መድረኮች በተለየ ትልቅ ዝግጅት መደረጉንም ገልፀዋል።
ዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ የዓለምን የሙቀት መጠን ለመቀነስ ምክክር የሚደረግበት ነው።
ጉባዔው በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚደርሱ ጉዳቶች መጨመር ለጉባዔው መጀመር ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ተጠቅሷል።