ለመካከለኛው ምስራቅ ቀጣና ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ልማት የጎላ አበርክቶ ይኖረዋልም ተብሏል
የ“አብርሃም ስምምነት” የዩኤኢን ሉዓላዊ የውሳኔ ባለቤነት የሚያረጋግጥ ነው
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በአሜሪካ ዋሽንግተን እንደሚፈረም የሚጠበቀው የ“አብርሃም ስምምነት/Abraham Accords” የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን ሉዓላዊ የውሳኔ ባለቤትነትን የሚያረጋግጥ ነው ተብሏል፡፡
ስምምነቱ ከአሁን ቀደም ከእስራኤል ጋር ስምምነትን ባደረገችው በዩኤኢ እና በእስራኤል እንዲሁም በእስራኤል እና በባህሬይን መካከል የሚፈረም ነው፡፡ በጋራ የሚፈርሙት የሶስትዮሽ ስምምነትም አለ፡፡
ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አብዱላሂ ቢን ዛይድ አል ናህያን፣ የባህሬይን አቻቸው አብዱላቲፍ አል ዛያኒ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተገኙበት ስምምነቱን ይፈርማሉም፡፡
ስምምነቱ ለመካከለኛው ምስራቅ ቀጣና ሰላምና መረጋጋት እንዲሁም ልማት የጎላ አበርክቶ ይኖረዋል ዋም እንደተሰኘው ሃገሪቱ የዜና አገልግሎት ዘገባ፡፡
ዩኤኢ በበኩሏ ስምምነቱ የራሷን የመወሰን ሉዓላዊ መብት ከማስጠብቅም በላይ ፖለቲካዊ አቋምንና የመደበኛ ግንኙነቶችን ልዩነት ታሳቢ አድርጎ ያለ አድልዎ የሚፈጸም እንደሆነ አሳስባለች፡፡
የፍልስጤምን ጥያቄዎች ከቀጣናዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ አመክንዮአዊ በሆነ መንገድ ምላሽ ለመስጠት እንደሚያስችልም ነው ያስታወቀችው፡፡
ዩኤኢ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ከእስራኤል ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማሻሻል ከሚያስችል ስምምነት ላይ መድረሷ የሚታወስ ነው፡፡