አሜሪካ ለአረብ ኢሚሬትስ ኤፍ-22 የተሰኘ የጦር ጀት እንደምትልክ አስታወቀች
የሆዚ ታጣቂ ቡድን በቅርቡ በአረብ ኢሚሬትስ ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙ ይታወሳል
የፔንታጎን ቃል አቀባዩ ጆን ክብርይ ”ሌላ ልንሰጣቸው የምንችለው የመከላከያ ድጋፍ ካላ ከኢሚሬትስ ጋር እየተነጋገርን ነው”ነው ብለዋል
የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር(ፔንታጎን) ቃል አቀባይ ጆን ክርብይ በገልፍ ቀጣና ያሉ አጋሮቿን ከሆዚ ታጣቂዎች ለመከላከል እንድትችል አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ጉልህ ስፍራ እንዲኖራት ትኩረት አድርጋ ትሰራለች ብለዋል፡፡
ቃል አቀባዩ ከአል-ሁራ ቻናል ጋር ባደረጉት ቆይታ አሜሪካ ሆዚ የሚፈጽመውን ድንበር ዘለል ጥቃት ለመከላከል እርምጃ እየወሰደች መሆኑን ተናግረዋል፡፡
እንደቃል አቀባዩ ገለጻ አሜሪካ ከኢሚሬትስ አየር ኃይል ጎን ሆኖ የሚዋጋ ዲስትሮየር ዩኤስኤስ ኮል እና ኤፍ-22 የተሰኘ ስኳድሮን ጄት መላኳን ገልጸዋል፡፡
የፔንታጎን ቃል አቀባዩ ጆን ክብርይ ”ሌላ ልንሰጣቸው የምንችለው የመከላከያ ድጋፍ ካላ ከኢሚሬትስ ጋር እየተነጋገርን ነው”ነው ብለዋል፡፡
አሜሪካ ሆዚ የሚሰነዝረውን ጥቃት በጥንቃቄ እንደምትመለከተው የገለጹት ቃል አቀባዩ ሳኡዲ አረቢያ እና አረብ ኤሚሬትስ በሆዚ የተጠቁት ኢራን በምትስጠው መሳሪያ ነው ብለዋል፡፡
ቃል አቀባዩ አሜሪካ መቼ ጥቃት ልትሰነር ትችላለች ለሚለው ጥያቄ መልስ ባይሰጡም፤ሆዚ ጥቃት መሰንዘሩን ማቆም እንዳለበት ትገልጻለች፡፡ አሜሪካ ኢራን የምታደርገው የማስታጠቅ እንቅስቃሴ ያሳስበኛል ብላለች፡፡
ምንም እንኳን ድምዳሜ ላይ ለመድረስ አስቸጋሪ ቢሆንም፤ ኢራን በኢራቅ ወስጥ ለእነዚህ ታጣቂዎች እና ሌላ ቦታ የምታደርገው ድጋፍ አካል ነው ብለዋል፡፡ መከላከለኛው ምስራቅ ትርጉም ያለው እንቅስቃሴ የምናደርገው ለዚህ ነው ይላሉ ቃል አቀባዩ፡፡
የየመኑ ሆዚ ታጣቂ ቡድን በቅርቡ በአረብ ኢሚሬትስ ላይ የሚሳኤል ጥቃት መፈጸሙ ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎም ኢሚሬትስ በቡድኑ ላይ የአጸፋ እርምጃ ወስዳላች፤ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች ሀገራት ለኢሚሬትስ አጋርነታቸውን አሳይተዋል፡፡