አረብ ኢሚሬትስ በዩክሬን ጉዳይ ላሳየችው ሚዛናዊ አቋም በሩሲያ ተመሰገነች
የኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አብደላህ ቢን ዛይድ ከሩሲያው አቻው ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተወያይተዋል
በአረብ ኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተመራ ልኡክ ለጉብኝት ሞስኮ ይገኛል
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በዩክሬን ጉዳይ ላይ ላንፀባረቀቸው ሚዛናው አቋም የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ አመሰገኑ።
የኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ አብደላህ ቢን ዛይድ አል ናህያን በሩሲያ ሞስኮ ጉብኝት እያደረጉ ነው።
በጉብኝቱ ወቅትም የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሼክ አብደላህ ቢን ዛይድን ተቀብለው አነጋግረዋል።
ሼክ አብደላህ በውይይቱ ኢሚሬትስ ከሩሲያ ጋር ያላትን ግንኙነት እያሳደገች ነው፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙትም ዘርፈ ብዙ እየሆነ ነው ብለዋል።
በቆይታቸውም ዩክሬን፣ ሶሪያ፣ የመን፣ ሊባኖስ እና ሌሎችንም ሀገራት ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፤ በሩሲያ እና ዩክሬን መካከል በመካሄድ ላይ ያለው ጦርነት ዲፕሎማሲያዊ መፍትሔዎች ሊፈለጉለት እንደሚገባም መናገራቸውንም ነው ያስታወቁት፡፡
ላቭሮቭ በበኩላቸው በዩክሬን ጦርነት ጉዳይ ላሳየችው ሚዛናዊ አቋም ዩኤኢን አመስግነዋል፡፡
በምክንያታዊነት ኢምሬትን ያወደሱት ላቭሮቭ የዩክሬን መንግስት ከእኛ ጋር ለመደራደር አሻፈር ማለቱን ለሼክ አብደላህ ገልጫለሁ ሲሉም ውይይቱን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስረድተዋል፡፡
ዩኤኢ ከዓረቡ ዓለም ያደገች መሆኗን በማከልም በአውሮፕላን ምርት እና በሌሎች ምጣኔ ሃብታዊ ጉዳዮች ላይ መተባበር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ መወያየታቸውንም ገልጸዋል፤ በመካከላቸው የ5 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ የንግድ ልውውጥ መኖሩን በመጠቆም፡፡
ሊቢያን ጨምሮ ስለ ፍልስጤም ጉዳይ እንዲሁም የሩሲያ ዲፕሎማቶች ዩኤኢን ስለሚጎበኙበት ሁኔታ መነጋገራቸውንም ላቭሮቭ ተናግረዋል፡፡