በዩኤኢ ሰዎች ከመኪናቸው ሳይወርዱ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የሚያደርጉበት ማእከል ተከፈተ
በዩኤኢ ሰዎች ከመኪናቸው ሳይወርዱ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ የሚያደርጉበት ማእከል ተከፈተ
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች(በዩኤኢ)ሰዎች ከመኪናቸው ሳይወርዱ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ለማድረግ የሚያስችል ማእከል መክፈቷን አስታውቃልች፡፡
የምርመራ ማእከሉን የከፈቱት ሼህ መሀመድ ቢን ዘይድ አል ንህያን፣ የአቡዳቢ ዘውዳዊ ልዑል እና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ አዛዥ ናቸው፡፡
በአምስት ደቂቃ ውስጥ የቫይረሱን መኖር ወይም አለመኖር ማሳወቅ የሚችለው ይህ ማእከል የተቋቋመው በአቡዳቢ የጤና አገልግሎት ኩባንያ ነው ተብሏል፡፡ በማእከሉ ለ600 ሰዎች ምርመራ ለማድረግ የሚያስችል አቅም አለው፡፡
በዩኤኢ የዚህ አይነት ሎሎች መሰል ማዕከላትን በ10 ቀናት ውስጥ 13 ተጨማሪ ከተሽከርካሪ ሳይወርዱ ምርመራ የሚያደርጉ ማእከላት ተዘጋጅተዋል፡፡
በማእከላቱ የቫይረሱ ምልክት የታየባቸው፣በእድሜ የገፉ ኣዛውንቶችና ነፍሰ ጡር ሴቶች እንዲሁም ሌላ በሽታ ያለባቸው ሰዎች የቅድሚያ ምርመራ አገልግሎት ይሰጣቸዋል፡፡
የምርመራ ማእከሉ በአረብኛና በእንግሊዝኛ የተዘጋጀና በ2 ደቂቃ ውስጥ ሞልተው በሚጨርሱት መጠይቆች ባሉት መተግበሪያ የታገዘ ነው፡፡ ሰዎች ለምርመራ ወደ ተቋሙ በሚመጡበት ጊዜ በሚያሽከረክሩት ተሽከርካሪ ኤፍኤም ራዲዮ በኩል የድምጽ መልእክት ይደረሳል፤ መልእክቱም በመኪናዎ ውስጥ ይቆዩና መታወቂዎን ያሳዩ የሚል ነው፡፡
በመቀጠልም መረጃውና ምዝገባው ከተረጋገጠ በኋላ የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ይካሄዳል፡፡