የሀገራቱ የንግድ ልውውጥም በ2022 ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር በላይ መድረሱን መረጃዎች ያሳያሉ
አረብ ኤምሬትስ ለኢትዮጵያ የምታደርገው የቀጥታ ድጋፍም ሆነ ኢንቨስትመንት በፍጥነት እየጨመረ ነው።
ሀገሪቱ ለኢትዮጵያ ያደረገችው ድጋፍ 5 ነጥብ 05 ቢሊየን ደርሷል።
ከዚህ ውስጥ 89 በመቶው ለተለያዩ የልማት ስራዎች የዋለ ሲሆን፥ በሀገሪቱ ሰላምና መረጋጋት እና ዘላቂ እድገት እንዲመዘገብ የምታደርገው ድጋፍም እየጨመረ መጥቷል።
አቡ ዳቢ ከምስራቅ አፍሪካዋ ሀገር ጋር የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነትም እንዲሁ ከፍተኛ እድገት በማስመዝገብ ላይ ነው።
ኢትዮጵያ ከነዳጅ ውጭ ባለ ግብይት የኢሚሬትስ ሁለተኛዋ ግዙፍ የንግድ አጋር ናት።
የሀገራቱ የንግድ ልውውጥ በ2022 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ 628 ሚሊየን ዶላሩ ኢትዮጵያ ወደ ኤምሬትስ የላካችው ነው።
የባህረ ሰላጤዋ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ኤምሬትስ በኢትዮጵያ የምታደርገው ኢንቨስትመንትም 2 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር መድረሱን መረጃዎች ያሳያሉ።
ዋና ዋና የኢንቨስትመንት ዘርፎቹም የመድሃኒት፣ አልሙኒየም፣ ምግብ እና ኬሚካል ማምረቻ ናቸው።
እንደ ዲፒ ወርልድ፣ ኤግል ሂልስ፣ ፋልኮን ኬሚካልስ፣ ጁልፋር እና አል ጋንዲ አውቶ ያሉ ግዙፍ ኩባንያዎቿም በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እያፈሰሱ ነው።