ፖለቲካ
ኢትዮጵያና አረብ ኤምሬትስ 2 ሺህ ሜጋ ዋት የፀኃይ ኃይል ማመንጫ ለመገንባት ስምምነት ተፈራረሙ
ኢትዮጵያ እና አረብ ኤምሬትስ በኢነርጂ ዘፍርና በሌሎችም ዘርፎች በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል
የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ ከጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ተወያየተዋል
አረብ ኢሚሬትስ እና ኢትዮጵያ 2 ሺህ ሜጋ ዋት የኤልክትሪክ ኃይል የማመንጨት አቅም ያለው ግዙፍ የፀኃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በግብፅ ለመገንባት ስምምነት ተፈራርመዋል።
የአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን በሀገሪቱ የሚገኙትን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድን በቃስር አል ሻቲ ቤት መንግስት ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይታቸውም ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች የበለጠ ተጠቃሚ በሚያደርጉ እና የሁለቱ ሀገራት ግንኙነቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተመካክረዋል።
ሁለቱ መሪዎች በተገኙበትም በኢትዮጵያ መንግስት እና በአረብ ኢምሬትሱ ማሳደር ኩባንያ መካከል የፀኃይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ስምምነት ተፈርሟል።
ስምምነቱንም የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና የኢንዱስትሪ እና የረቀቁ ቴክኖሎጂዎች ሚኒስትር ዶ/ር ሱልያን ቢን አህምድ አል ጃብር ፈርመውታል።
በስምምነቱ መሰረት ማሳዳር 2000 ሜጋ ዋት የፀኃይ ኃይል ማመንጫ በኢትዮጵያ የሚገነባ ሲሆን፤ በመጀመሪያው ምዕራፍም 500 ሜጋ ዋት የሚገነባ ይሆናል።