“የዛሬው የዩኤኢ ድጋፍ ድንገተኛ ህክምናን ከማጠናከር አንጻር የሚመሰገን ነው”- ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ ጤና ሚኒስትር
ድጋፉ ድንገተኛ የአምቡላንስ ህክምናን ለማጠናከር እንደሚያስችልም ዶ/ር ሊያ ገልጸዋል
ዩኤኢ ለኢትዮጵያ የ50 አምቡላንሶች ድጋፍ አድርጋለች
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (ዩኤኢ) ለኢትዮጵያ የ50 አምቡላንሶች ድጋፍ አደረገች፡፡
ድጋፉ በኤምሬት ቀይ ጨረቃ ማህበር (UAE Red Crescent) በኩል የተደረገ ነው፡፡ ማህበሩ በተለያዩ በጎ አድራጎት ስራዎች ላይ የተሰማራ ድርጅት ነው፡፡
የአምቡላንሶቹ ርክክብ ዛሬ ማክሰኞ ጥቅምት 9 ቀን 2014 ዓ/ም በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተፈጽሟል፡፡
ዩኤኢ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንደማይገባ ገለጸች
በቁልፍ ርክክብ ስነ ስርዓቱ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አምባሳደር መሃመድ ሳሊም አል ራሺድ እንዲሁም የኤምሬት ቀይ ጨረቃ ማህበር ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
ስለ ድጋፉ ያመሰገኑት ዶ/ር ሊያ አምቡላንሶቹ ድንገተኛ የአምቡላንስ ህክምናን ለመስጠት የሚያስችሉ የህክምና መሳሪያዎች የተሟሉላቸው ናቸው ብለዋል፡፡
ይህ መሆኑ ለአምቡላንስ የህክምና አገልግሎቱ ትልቅ ድጋፍ እንደሚያደርግም ሚኒስትሯ የተናገሩት፡፡
“የዛሬው የዩኤኢ ድጋፍ ድንገተኛ ህክምናን ከማጠናከር አንጻር የሚመሰገን ነው”ም ብለዋል፡፡
ዩኤኢ ለትግራይ ክልል የሚሆኑ የምግብ እርዳታዎችን የጫነ አውሮፕላን ላከች
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ከአሁን ቀደምም ለኢትዮጵያ የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጓ የሚታወስ ነው፡፡