አረብ ኢሚሬትስ በዓለም ላይ መረጋጋትን መፈጠር እንዳለበት ታምናለች- አል-ቦዋርዲ
በአለም አቀፍ የመከላከያ ኮንፈረንስ በአረብ ኢሚሬትስዋ አቡ ዳቢ እየተካሄደ ነው
በኮንፈረንሱ ላይ የቀጠናው እና የዓለም ሀገራት የመከላከያ አመራሮችና ተወካዮች ተሳትፈዋል
አረብ ኢሚሬትስ በዓለም ላይ መረጋጋትን መፈጠር እንዳለበት እንደምታምን የሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ደዔታ ሞሃመድ ቢን አህመድ አል-በዋርዲ አስታወቁ።
በአለም አቀፍ የመከላከያ ኮንፈረንስ በአረብ ኢሚሬትስዋ አቡ ዳቢ በመካሄድ ላይ ዪገኝ ሲሆን፤ በኮንፈረንሱ ላይ የቀጠናው እና የዓለም ሀገራት የመከላከያ አመራሮችና ተወካዮች ተሳትፈዋል።
ሞሃመድ ቢን አህመድ አል-በዋርዲ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ሀገራቸው በቀጣናው እና በአለም ላይ ፀጥታና መረጋጋትን ማስፈን አስፈላጊ መሆኑን እንደምታምን አረጋግጠዋል።
አሁን ያለንበት ዘመን ከፍተኛ የሆነ ስጋት እና አመጽ የሞላበት ነው ያሉት ሚኒስትር ደዔታው የዚህ መነሻም በፈጣን እድገት እና በላቁ ቴክኖሎጂዎች ላይ በመተማመን እንደሆነም ጠቅሰዋል።
"ደህንነትንማስፈን ቅድሚያ የምንሰጣቸው ጉዳዮች ቀዳሚው ነው ያሉት አል-ቦዋሪ፤ ይህም ማህበረሰባችን በተጠበቀ አካባቢ እንዲኖሩ መንገድ የሚከፍት ነው ብለዋል።
አል-ቦዋርዲ አክለውም፤ ግጭቶችን በውይይት እና በመግባባት መመፍታት ዓለም አቀፋዊ ሰላም እንዲሰፍን እንዲሁም እድገትና ብልጽግናን ያመጣል ሲሉም ተናግረዋል።
አል ባዋርዲ ሀገራት በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የቀረበውን የመቻቻል እና የሰላም አብሮ የመኖር ሞዴል እንደቀበሉም ጥሪ አቅርበዋል።
የአለም አቀፍ የመከላከያ ኮንፈረንስ በአረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት እና በጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን አስተባባሪነት የሚካሄድ ነው።
አቡ ዳቢ ዓለም አቀፍ የመከላከያ ኮንፈረንስ ላይ 1 ሺህ 800 ዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪዎች እንደሚሳተፉበትም ተመላክቷል።