የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የኢነርጂ ላኪ ሆና እንደምትቀጥል ገለጸች
አረብ ኢሚሬትስ ለታዳሽ ኃይል በቢሊዮን ዶላሮች ፈሰስ የምትዳርግ ሀገር መሆኗ ይታወቃል
አረብ ኢሚሬትስ በታዳሽ ኃይል ላስመዘገበችው እድገት የፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ሚና ከፍተኛ ነው ተብሏል
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የኢነርጂ ላኪ ሆና እንደምትቀጥል የሀገሪቱ የአየር ንብረት ለውጥ እና የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ሜሪየም አል ሙሀይሪ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሯ በሙኒክ የጸጥታ ኮንፈረስን ላይ በነበረው ውይየት መድረክ እንደተናገሩት አረብ ኤሚሬትስ በኃላፊነት ስሜት እና ካርበንን ለመቀነስ የተሻለውን መንገድ ትጠቀማለችም በለዋል፡
እንደ የታዳሽ ኃይል ፕሮጄክቶችን የሚሰራው ማስዳር እና የኃይል ኩባኒያዎች ስብስብ የሆነው የአቡ ዳቢ ብሔራዊ የነዳጅ ኩባንያዎች (ADNOC) የሚያከናውኗቸው ተግባራት ለዚህ በአብነት የሚጠቀሱ መሆናቸውም ተናግረዋል፡፡
ቀጣዩ አመት 2023 እጅግ በጣም ወሳኝ እንደሆነ እናውቃለን ያሉት ሚኒስትር ሜሪየም፤ ከነበረው የተሻለ እርምጃ ለመጓዝም የፋይናንስ ሴክተሩ ክፍት ማድረግ ወሳኝ መሆኑም አንስተዋል፡፡
ሀገራቸው ኢነርጂን ለመላክ በረጅሙ አቅዳ እየሰራች መሆኗንም ገልጸዋል፡
“አሁን ላይ ወደ ውጭ የምንልከው የኢነርጂ አይነት እየተቀየረ ነው፤ ወደፊትም እየተሻሻለ የሚሄድ ይሆናል”ም ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሯ አረብ ኢሚሬተስ ታዳሽ ኃይልን እውን በማድረግ አሁን ለደረሰችበት እድገት የአሁኑ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ ሚና ከፍተኛ እንደነበርም በመድረኩ አንስተዋል፡፡
የአሁን ፕሬዝዳንታችን በ2015 “ዛሬ በትክክል ኢንቨስት ካደረግን ከጥቂት አመታት በኋላ የመጨረሻውን የነዳጅ በርሜል ወደ ውጭ እንልካለን፡ ብለውን ነበር፡፡ ይህ ያሉት በ 2015 ነበር ፤እየሆነ ያለውም እሱ ነው” ሲሉም ነው የፕሬዝዳንቱን የአመራርና በረጅሙ አቅዶ የመስራትና የመምራት ብቃት የገለጹት ሚኒስትሯ፡፡
በመጨረሻም ኮፕ-28 ቃል ኪዳኖች ወደ ተግባር የሚለወጡበትና ቁልፍ ውሳኔዎች የሚተላለፉበት እንዲሆን ሁሉም አካላት ጉዳዩን የራሳቸው ማድረግ ይጠበቅቸዋል ብለዋል፡፡
አረብ ኢሚሬትስ ለታዳሽ ኃይል (ኢነርጂ) ዘርፉ በምትሰጠው ትኩረት የዓለም አቃፍ ታዳሽ ኃይል ዓመታዊ ጉባኤ ቋሚ አዘጋጅ ናት፡፡
የፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነትን ተቀብለው ከፈረሙና ግዙፍ የጸሃይ ኃይል አማራጮችን በመገንባት ኢነርጂን በርካሽ ከሚያቀርቡ የአረቡ ዓለም ሀገራት መካከልም ቀዳሚዋ ነች።
ሀገሪቱ በ6 አህጉራት በሚገነቡ የታዳሽ ኃይል ልማት ፕሮጄክቶች ላይ ወደ 20 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ፈሰስ አድርጋ በመስራት ላይ መሆኗም ይታወቃል፡፡