ሩሲያ የጉዞ እገዳ የተጣለባቸው ዜጎች ፖስፖርታቸውን እንዲያስረክቡ የሚያስገድድ ህግ አወጣች
እንደህጉ ከሆነ እገዳው ከተነሳ በኋላ የፖስፖርቱ ባለቤት ማመልከቻውን እንዳጠናቀቀ ይመለስለታል
በህጉ መሰረት ባለስልጣናት በወታደሮች፣ በፌደራል የደህንነት ሰራተኞች፣ በወንጀለኞች እና የመንግስት ሚስጥር በሚያውቁ ባላቸው ሰዎች ላይ የጉዞ እገዳ መጣል ይችላሉ
ሩሲያ የጉዞ እገዳ የተጣለባቸው ዜጎች ፖስፖርታቸውን እንዲያስረክቡ የሚያስገድድ ህግ አወጣች።
በሀገሪቱ የወጣው አዳስ ህግ ወደ ውጭ እንዳይጓዙ እግድ የተጣለባቸው ሩሲያውያን በተነገራቸው በአምስት ቀናት ውስጥ ፖስፖርታቸውን ለመንግስት ያስረክባሉ።
በዚህ ህግ መሰረት የሩሲያ ባለስልጣናት በወታደሮች፣ በፌደራል የደህንነት ሰራተኞች፣ በወንጀለኞች እና የመንግስት ሚስጥር በሚያውቁ ወይም የተለየ ጠቀሜታ ያለው መረጃ ባላቸው ሰዎች ላይ የጉዞ እገዳ መጣል ይችላሉ።
ከዜጎች የተመለሰው ፖስፖርት እገዳውን በጣለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ወይም በሀገር ውስጥ ደህንነት ይቀመጣል።
እንደህጉ ከሆነ እገዳው ከተነሳ በኋላ የፖስፖርቱ ባለቤት ማመልከቻውን እንዳጠናቀቀ ይመለስለታል።
በወታደራዊ ወይም በሌላ የሲቪል ስራ ላይ ያሉ እና ጊዜያዊ እግድ የተጣለባቸው ዜጎች እገዳው ሲነሳ ፖስፖርታቸውን ለመውሰድ፣ የተሰጣቸው የአገልግሎት ጊዜ ማለቁን የሚያሳይ መረጃ ይዘው መቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ህጉ ጠቅሷል።
ሮይተርስ ፋይናንሻል ታይምስ ባለፈው ሚያዛያ ላይ ያቀረበውን ሪፖርት ጠቅሶ እንደዘገው የሩሲያ የደህንነት መስሪያ ቤት የከፍተኛ ባለስልጣናት እና የመንግስት ኩባንያዎች ዋና ስራ አስፈጻሚ ፖስፖርቶችን ወርሰዋል።