
የዩክሬን-ሩሲያ ድርድር የታገዱ ገንዘቦችንም ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል
የሩሲያን ገንዘብ ያገዱ የዓለማችን ሀገራት እነማን ናቸው?
ሩሲያ ጦሯን ወደ ዩክሬን ልዩ ዘመቻ በሚል ለሁለት ሳምንት ውስጥ ለማጠናቀቅ የጀመረችው ጦርነት ሶት ዓመት አልፎታል፡፡
ጦርነቱ መከሰቱን ተክተሎ ሩሲያ ጦሯን ከዩክሬን ግዛቶች እንድታስወጣ በሚል በሞስኮ ላይ ከ12 ሺህ በላይ ማዕቀቦች ተጥሎባታል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በውጭ ሀገራት ያሉ የሩሲያ ሀብት እንዳይንቀሳቀስ የታገደ ሲሆን በአጠቃላይ ግማሽ ትሪሊዮን ዶላር ገንዘብ ታግዷል፡፡
ቤልጂየም ብቻ 254 ቢሊዮን ዶላር የሩሲያን ገንዘብ ስታግድ፣ ፈረንሳይ 72 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም ጃፓን 58 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ ማገዷን አርቲ ዘግቧል፡፡
ሩሲያ በአንጻሩ 300 ቢሊዮን ዶላር የምዕራባዊንን ገንዘብ አግዳለች የተባለ ሲሆን ጦርነቱን ለማስቆም እየተደረገ ባለው ድርድር ላይ የታገዱ ገንዘቦች ጉዳይ አንዱ የድርድር አጀንዳ ሆኗል፡፡
ይሁንና ከፍተኛ ገንዘብ የታገደበት የአውሮፓ ህብረት በድርድሩ ላይ እየተሳተፈ አለመሆኑ ጦርነቱ ላይቆም ይችላል የሚል ስጋት ደቅኗል፡፡