አረብ ኢምሬትስ በሰብአዊ መብት ዘርፍ ያስመዘገበቻቸውን ስኬቶች ለካውንስሉ አቀረበች
አረብ ኢምሬትስ የኮኘ 28ን የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ታስተናግዳለች
አረብ ኢምሬትስ በሰብአዊ መብት ዘርፍ ያሰገኘቻቸውን ውጤቶች ለሰብአዊ መብት ካውንስል አቅርባለች
አረብ ኢምሬትስ በሰብአዊ መብት ዘርፍ ያሰገኘቻቸውን ውጤቶች ለሰብአዊ መብት ካውንስል አቅርባለች።
የአረብ ኢምሬትስ የማህበረሰብ ልማት ሚኒስትር የሆኑት ሻማ ቢንት ሱሃሊ አል ማዝሮይ እንደተናገሩት አረብ ኢምሬትስ ሁሉም የመንግስት እቅዶች ለሰው ቅድሚያ የሚሰጡ እና የሰው ልጅ በምቾች እና በክብር እንዲኖር የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።
ሚኒስትሯ የአረብ ኢምሬትስን ብሄራዊ ሪፖርት ለሰብአዊ መብት ካውንስል አቅርበዋል።
አለምአቀፉ የሰብአዊ መብት ጥምረት ፕሬዝደንት አረብ ኢምሬትስን ማድነቁንም ሚኒስትሯ ተናግረዋል።
ሚኒስትሯ እንደተናገሩት አረብ ኢምሬትስ ለሰብአዊ መብት ጉዳይ ትልቅ ትኩረት በመስጠት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት ያላትን ልምድ እንዲቀስሙ እድል ሰጥታለች ብለዋል።
እንደሚኒስትሯ ገለጻ አረብ ኢምሬትስ በሰብአዊ መብት ዙሪያ ህጎችን እና አሰራሮችን በማሻሻል የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ቁርጠኛ ነች።
በሰብአዊ መብት ላይ መሻሻል ለማምጣት አቅም እና የተመቻቸ ሁኔታ እንደሚያስፈለግ የገለጹት ሚኒስትሯ ሰዎች በተስማሚ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ እንዲኖሩ ማድረግ ሌሎች ሰብአዊ መብቶችም እንዲከበሩ ይረዳል ብለዋል።
ሚኒስትሯና ሀገራቸው ሁል ጊዜ ለሰው ቅድሚያ የምትሰጥ ስለሆነች ሁሉም እቅዶቿ የሚተገበሩት ለሰው ልጅ ክብር እና ምቾት እንዲሰጡ ተደርገው መሆኑን ተናግረዋል።
ሚኒስትሯ ከፈረንጆቹ 2018 እስከ 2022 መጨረሻ በሰብአዊ መብት ዙሪያ ወሳኝ የሚባል መሻሻል አሳይቷል ብለዋል።
አረብ ኢምሬትስ የኮኘ 28ን የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ ታስተናግዳለች።