አረብ ኢምሬት በኩዌት ኢምር ሞት ምክንያት የሶስት ቀናት ሐዘን አዋጀች
ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በኩዌት ኢምር ሼክ ናዋፍ አል አህመድ አል ጃቢር ሞት ምክንያት ብሔራዊ የሀዘን ቀን አውጀዋል
አረብ ኢምሬት ሰንደቅ አላማዋ ለሶስት ቀናት ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ አስታውቃለች
አረብ ኢምሬት በኩዌት ገዢ ሞት ምክንያት የሶስት ቀን ሐዘን አዋጀች፡፡
የኩዌት ኢምር ሼክ ናዋፍ አል አህመድ አል ጃቢር ባሳለፍነው እሮብ ዕለት ነበር ህመም አጋጥሟቸው ለሕክምና ወደ ሆስፒታል ያመሩት፡፡
ላለፉት ቀናት ሕክምና ላይ የነበሩት ሼክ ናዋፍ በዛሬው ዕለት ሕይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል፡፡
የተባበሩት አረብ ኢምሬት ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በኩዌት ገዢ ሼክ ናዋፍ ህልፈት ህይወት ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በኩዌት ገዢ ሼክ ናዋፍ አል አህመድ አል ጃቢር ህልፈተ ህይወት ምክንያት የሶስት ቀናት ብሔራዊ ሀዘን ማወጃቸውን አስታውቀዋል፡፡
በዚህም ምክንት በመላው የተባበሩት አረብ ኢምሬት እና ኢምባሲዎች የሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ እንደሚውለበለብ ኢምሬት ዜና አገልግሎት (ዋም) ዘግቧል፡፡
የኩዌት ገዢ ሼክ ናዋፍ አል አህመድ አል ጃቢር በተወለዱ በ86 ዓመታቸው በሕመም ምክንያት ህይወታቸው አልፏል ተብሏል፡፡
ሼክ ሞሃመድ ቢን ዛይድ አረብ ኢምሬትስ ለአየር ንብረት መፍትሄዎች የ30 ቢሊዮን ዶላር ፈንድ ማቋቋሟን አስታወቁ
ሼክ ናዋፍ አል አህመድ አል ጃቢር በፈርነጆቹ 2020 ላይ የኩዌት ገዢ ሆነው ከመሾማቸው በፊት የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትርን ጨምሮ በበርካታ ወታደራዊ እና የሲቪል አስተዳድር ተቋማትን ለዓመታት ሲመሩ ቆይተዋል፡፡
እንዲሁም የመከላከያ ሚኒስትር፣ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ሚኒስትር እና ሌሎች መንግስታዊ የሀላፊነት ቦታዎችን ተረክበው ሲመሩ እንደቆዩም ተገልጿል፡፡