ፖለቲካ
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በጣሊያን ጉብኝት ሊያደርጉ ነው
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት መሀመድ ቢን ዛይድ በቀጣይ ሳምንት ሰኞ በጣሊያን ይፋዊ የስራ ጉብኘት ሊያደርጉ ነው

ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በጉብኝታቸው ወቅት ከጣሊያን ፕሬዝደንት ሰርጂኦ ማታሬላና ከጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋር ይወያያሉ ተብሏል
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት መሀመድ ቢን ዛይድ በቀጣይ ሳምንት ሰኞ በጣሊያን ይፋዊ የስራ ጉብኘት ሊያደርጉ ነው።
ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ በጉብኝታቸው ወቅት ከጣሊያን ፕሬዝደንት ሰርጂኦ ማታሬላና ከጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋር በተለያዩ የትብብር ዘርፎች በተለይም በኢኮኖሚ፣ በኢንቨስትመንት፣ በታዳሽ ኃይልና በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ ዙሪያ ይወያያሉ ተብሏል።
ትብብሮቹ የሚደረጉት በአረብ ኢምሬትስና በጣሊያን መካከል ባለው ስትራቴጂካዊ የግንኙነት ማዕቀፍ ስር እንደሚሆን ተገልጿል።