ከሁለት ዓመት በፊት የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ፣ እስራኤልና ሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በዋይት ሀውስአመቻችነት የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል
የእስራኤል ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያንን መክረዋል።
የእስራኤል ፕሬዝዳንት በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያንን በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ ብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም "አስደናቂው የአብርሃም ስምምነት ለቀጣናችን ትልቅ ስጦታ ነው” ያሉ ሲሆን፤ በቀጣይም በመካከላችን ያለውን አጋርነት ለማጠናከር በጋራ እንሰራለን ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ሄርዞግሌ “ሌሎች ሀገራት ወደ ሰላም ክበቡ እንደሚቀላቀሉ ተስፋ አደርጋለሁ" ብለዋል።
መሪዎቹ በውይይታቸው በሁለቱ ሀገራት የትብብር ግንኙነት እና ልማትን በማስፋፋት መንገዶች ላይ መክረዋል ነው የተባለው።
በአጠቃላይ ለክልሉ ህዝቦች ሰላምና ብልፅግ እንዲሁም ተጠቃሚነት ሲባል በተለያዩ ጉዳዮች ላይም ሀሳብ መለዋወጣቸው የተዘገ ሲሆን መሪዎቹ በሀገራቱ የጋራ የጥቅም ጉዳዮች ላይም ስለመምከራቸው ተነግሯል።
እ.ኤ.አ. መስከረም 15፤ 2020 የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ እና እስራኤል በዋይት አመቻችነት የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል። ስምምነቱ ለሰላም መንገድ የከፈተ ታሪካዊ ስምምነት ተብሏል።
የአብርሀም ስምምነት ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ ጠቃሚ የሆኑ ደረጃዎችን በማሳለፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤቶች ተመዝግበዋልም ነው የተባለው።
የአብርሃም ስምምነት በእስራኤል፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ በባህሬን፣ በሱዳን እና በሞሮኮ መካከል ያሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶችን የሚያስተካክል ስምምነት ነው።
በአምስት አጭር ወራት ውስጥ እነዚህ አራት የአረብ ሀገራት ከእስራኤል ጋር ሰላም ለመፍጠር ግብፅ እና ዮርዳኖስ ተቀላቅለዋቸዋል።
ስምምነቱ አብርሃም የተባለው የአይሁድ፣ የክርስትና እና የእስልምና ኃይማኖት ለማማከልና ለማስተሳሰር እንደሆነ ተነግሯል።